ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ በ2012 የበጀት ዓመት ከታክስ በፊት 1.9 ቢሊዮን ብር አትርፊያለሁ ሲል ገለጸ፡፡
ብሔር ተኮር ሆነው ከተቋቋሙትና ዘረኝነትን በተንጠላጠለ አሠራር በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ መሆን ከቻሉ ባንኮች መሀል የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ አንዱ መሆኑ ይታወቃል።
ተገኘ የተባለው ትርፍ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር፤ በእጥፍ ያህል እንደተሰላ የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ደርቤ አስፋው ሁሩሳ ተናግረዋል።
የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ የ2012 በጀት ትርፍ በሀገሪቱ ካሉ ባንኮች በ3ኛ ደረጃ ላይ እንዳስቀመጠው ከፕሬዝዳንቱ መግለጫ መረዳት ችለናል።
በ2011 ዓ.ም የባንኩ አጠቃላይ ሀብት ከነበረበት 47.79 ቢሊየን ብር የ11.13 ቢሊየን ብር ጭማሪ በማሳየት፣ በ2012 ዓመት 52.92 ቢሊየን ብር እንደደረሰም ታውቋል።
በተመሳሳይ የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ 45.52 ቢሊየን ብር መድረሱን የገለጹት የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ደርቤ፤በደንበኛ ብዛት ከግል ባንኮች ቀዳሚ መሆኑን ጠቁመው፣ አሁን ላይ የባንኩ የደንበኞች ብዛት 6 ሚሊየን 250 ሺኅ መሆኑን እና የባንኩ የተከፈለ ካፒታሉ 3 ቢሊየን ብር መድረሱን ገልጸዋል።
በተለይም በኦሮሚያ ክልል ሁሉም ዞኖች በስፋት እየተንቀሰቀሰ የሚገኘው ኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ የቅርንጫፎቹ ብዛት 420 ደርሷል።