653 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ፣ 11 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል

653 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ፣ 11 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት በኢትዮጵያ በተለይም በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ በከፍተኛ ሁኔታ ከመጨመሩ ባሻገር፣ የሞት ሪከርዱም እያንሰራራ ሄዷል።

የጤና ማኒስትር ባወጣው የዛሬ ሪፖርት ባለፋት 24 ሰዐታት ለ6 ሺኅ 503 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 653 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተገልጿል።
በተመሳሳይ ሁኔታ 11 ሰዎች ባለፋት 24 ሰዐታት በቫይረሱ ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን በአጠቃላይ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች በሀገራችን 239 ደርሷል።
እንደ ሚኒስቴር መ/ቤቱ መግለጫ እስካሁን በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 15 ሺኅ 200 ደርሷል።

LEAVE A REPLY