ህወሓት የትግራይን ሕዝብ ለማስተዳደር ሳይሆን ለመግዛት እየደከመ መሆኑን ታዬ ደንደኣ ገለጹ

ህወሓት የትግራይን ሕዝብ ለማስተዳደር ሳይሆን ለመግዛት እየደከመ መሆኑን ታዬ ደንደኣ ገለጹ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || አንድ ጊዜ የበላይነትን የለመደ አካል “እኩል ሁን ” ሲባል የተዋረደ ይመስለዋል ሲሉ የኦሮሚያ ክልል፣ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታዬ ደንደኣ ተናገሩ።

በህወሓት ዘመን በኦነግ አባልነት ተፈርጀው ለተደጋጋሚ እስረ ተዳርገው የነበሩት አቶ ታዬ ደንደኣ “ህወሓቶች እኛ በታሪክ ካለን አስተዋጽዖ አንጻር የተለየና የበለጠ ቦታ፤ ሥልጣንና ኢኮኖሚ ይገባናል ብለው በግልጽ ያነሳሉ። ከዚህ ባለፈም በዚህ አገር ውስጥ በአንድ በኩል የተዘረፉና የተሰረቁ በርካታ ነገሮች አሉ፤ እናም ይሄ ለውጥ መሰረቱን ይዞ በትክክለኛው አቅጣጫ የሚዘልቅ ከሆነ ምናልባትም ነገ ተጠያቂነት ይመጣል የሚል ስጋትም አለባቸው።” ሲሉ መቀለ የመሸገው ቡድን በግራ መጋባት ውስጥም እንደሚገኝ ገልጸዋል።
እነዚህ ኃይሎች ያለፈውን ትተን እሱ ስለማይጠቅመን መልካም ነገሮችን በማጎልበት የተበላሹትን ለማስተካከል ከዚህ ጀምረን እንስራ፣ጰየይቅርታ መንገድ እንከተል የሚለውን ለማመን አልፈለጉም ሲሉ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ የተናገሩት ታዬ ደንደኣ፤ “ለማመን ያልፈለጉት  እነርሱ ስለማይታመኑ ፣ ሁሉም እንደዛው ስለሚመስላቸው ነው ። እነርሱ በአፋቸው የሚሉት ሌላ፤ በልባቸው የያዙት ሌላ ስለሆነ ሰው በቅንነት በዚህ ደረጃ ነው ለኢትዮጵያ የሚያዋጣው ብሎ ቢነገር ከራሳቸው አንጻር ስለሚመነዝሩት ይሄንንም ሊያምኑ አልቻሉም።” በማለት ሀቁን ለማስረዳት ሞክረዋል።
ህወሓቶች እርስ በርሱ እየተጠራጠሩ ነው የመጡት ያሉት አቶ ታዬ ደንደኣ፤ “ለትግራይ ሕዝብ  በስሙ ነገዱበት እንጂ ለ27 ዓመታት እነርሱ የሚሠሩት ለራሳቸው ስለሆነ ይህችን ኢትዮጵያ እኛ ካልገዛናት፤ እኛ እንደፈለግን የማናደርጋት ከሆነች  ትጥፋ በሚል እየተንቀሳቀሱ ነው” ሲሉ የህወሓትን ጸብ አጫሪነት ለማሳየት ሞክረዋል።
አሁንም ሥልጣን ለመቆጣጠር ፍላጎት አለ፤ ያ የማይሳካ ከሆነ ደግሞ ኢትዮጵያ እንደ አገር መቀጠል የለባትም፤ እኛ የዛን ክልል ማህበረሰብ ለይተን እንገዛዋለን (እናስተዳድረዋለን ሳይሆን እንገዛዋለን ነው)፤ ከማለት ባሻገር፤ ሀገር ሲቃጠል ዳር ሆነን እናያለን የሚል ስሜት በወያኔው ቡድን በኩል እንዳለ ገለጸዋል።
“የሴራ ፖለቲካ የህወሓት የተካነበት ነው። የሚያውቁት የሚናገሩትም ይሄንኑ ነው” የሚሉት አቶ ታዬ፣ “ደርግ የመሬት ላራሹ ጥያቄን ሲመልስ ሁሉም የኢትዮጵያ አርሶአደሮች በአዎንታ ነው የተቀበሉት። ያንንም ትግራይ ላይም ጭሰኛ የነበሩ ዜጎች መሬት ሲያገኙ ደርግን ተቀብለውታል” በማለት በምሳሌ አብራርተዋል።

LEAVE A REPLY