የጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞች ሹመት ፀደቀ

የጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞች ሹመት ፀደቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || መደበኛ ጉባዔውን ሲያካሂድ የሰነበተው የአማራ ክልላዊ መንግሥት ከጠቅላይ ፍርድ ቤት እስከ መጀመሪያ ፍርድ ቤት ድረስ ያሉ የተለያዮ የዳኝነት ሹመቶችን ሰጥቷል።

በአማራ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 15ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ የተከበሩ አቶ አብዬ ካሳሁን (የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት) ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኝነት ያቀረቧቸዉን የ14 ዳኞች ሹመትን ምክር ቤቱ ተቀብሎ በአንድ ተቃውሞና በአብላጫ ድምፅ አፅድቆታል።
በተመሳሳይ ዐራት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቶችን እና 166 አዲስ የወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞችን በሙሉ ድምጽ በማጽደቅ መሾማቸውን ተከትሎ በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።
ሹመት ከተሰጣቸዉ 14ቱ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች መሀል ሦስቱ ሴቶች ሲሆኑ፣ አዲስ ከተሾሙት ከ166ቱ የወረዳ ዳኞች መካከልም 63 ሴቶች ሲሆኑ  ሁለቱ ዓይነ ስዉራን እንደሆኑም ታውቋል።

LEAVE A REPLY