ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አንድ 100 ስመ ጥር አፍሪካውያን መካከል አንዱ በመሆን ተመረጡ

ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አንድ 100 ስመ ጥር አፍሪካውያን መካከል አንዱ በመሆን ተመረጡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የፈረንጆቹ 2020 ፣ አንድ መቶ (100) ስመ ጥር አፍሪካውያን መካከል አንዱ ሆነው መመረጣቸው ታወቀ።

ሪፒዩቴሽን ፖል ኢንተርናሽናል የተሰኘው ተቋም የፈረንጆቹ 2020 በተለያዩ የሙያ መስኮች ስመ ጥር የሆኑ 100 አፍሪካውያንን ዝርዝር ይፋ ሲያደርግ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመሪዎች ደረጃ አንዱ ሆነው መካተታቸው  ተገልጿል።
የላይቤሪያው ምክትል ፕሬዝዳንት ጀዌል ሃዋርድ፣ የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ ሺሴኬዲ፣  የዓለም ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንት ሀፊዝ ጋነምን ጨምሮ በተለያዩ ዓለም  ዐቀፍ ተቋማት የሚሠሩ አፍሪካውያን እንደተካተቱ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በተጨማሪም የሰብኣዊ መብት ተሟጋቾች፣ ጸሐፊዎች፣ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች እና የሥራ እድል ፈጣሪዎችን ጨምሮ በበርካታ የሙያ ዘርፎች የተሠማሩ አፍሪካውያን የተካተቱበት መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።
የአፍሪካ ዘላቂ ልማት ግብ ማዕከል ዳይሬክተር ጀነራል የሆኑት ኢትዮጵያዊው በላይ በጋሻውም ከ100 ስመ ጥር አፍሪካውያን መካከል አንዱ ሆነዋል። ከእርሳቸው በተጨማሪ ሥራ ፈጣሪዋና የሶል ሬብልስ ባለቤት ቤተልሔም ጥላሁን በቢዝነስ ሥራ እድል ፈጠራ ዘርፍ በፈረንጆቹ 2020 ከ100 ስመ ጥር አፍሪካውያን መካከል አንደኛዋ መሆኗ ተረጋግጧል።

LEAVE A REPLY