ኢትዮጵያ ነገ ዜና ||  የብልፅግና ፓርቲ “ወላጅ” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር ተወያዮ።

ውይይቱ በመንግሥት እና በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል በወቅታዊ የአገሪቱ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ከመሆኑ ባሻገር፤ በቀጣይም ሀገራዊ ምርጫን በሚመለከት ከዚህ በፊት ከተደረገው ምክክር የቀጠለ ውይይት እንደተደረገበት ታውቋል።
በመንግሥትና በፖለቲካ ፓርቲዎች መሀል የተደረገው ውይይት  ሰባት በሚደርሱ አጀንዳዎች ላይ ምክክር ለማድረግ  በቅድሚያ ከስምምነት ላይ የተደረሰ ሲሆን፣ በቅድሚያ ግን ውይይት የሚደረግባቸው አራት አጀንዳዎች ተለይተው በእነርሱ ላይ ሠፊ ምክክር ተካሂዷል።
በዚህም መሠረት በቅድሚያ ሀገራዊ መግባባት ላይ ውይይት ለማካሄድ የተስማሙ ሲሆን፤ በዚህም ጉዳይ ላይ ገለጻ ለማድረግ እና ለማወያየት ከተለያዩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ሰዎች መመረጣቸውን የደረሰን መረጃ  ያሳያል።

LEAVE A REPLY