በጉባ በርካታ አማሮችን የገደሉት 20 ታጣቂዎች ከነመሣሪያቸው በቁጥጥር ሥር ዋሉ

በጉባ በርካታ አማሮችን የገደሉት 20 ታጣቂዎች ከነመሣሪያቸው በቁጥጥር ሥር ዋሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከሦስት ቀን በፊት ሐምሌ 20/2012 ዓ.ም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ፣ ጉባ ወረዳ ጥቃት የፈጸሙ 20 ታጣቂዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰማ።

13 የአማራ ተወላጆችን የገደሉትና በርካታ ሰዎችን ያቆሰሉት ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር የዋሉት ትናንት መሆኑን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ሠላም ግንባታ እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ሓላፊ አቶ አብዱላዚዝ መሃመድ  ለቢቢሲ ገልጸዋል።
 ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ከመፈጸማቸው በፊት የመንግሥት የጸጥታ ኃይል እርምጃ እየወሰደባቸው እንደነበር የጠቆሙት ሓላፊው፤ የእርምጃውን መጠንከር ተከትሎ የተበታተኑት ኃይሎች 13 ሰዎች ላይ ግድያ መፈጸማቸውን አረገዘች ግጠዋል።
ከጥቃቱ በኋላ በተደረገ የክትትልና የቁጥጥር ሥራ 20 ሰዎች ትናንት መያዛቸውን የጠቆሙት አቶ አብዱላዚዝ፤ ግለሰቦቹ ሲጠቀሙባቸው የነበሩ 12 መሣሪያዎችም መያዛቸውን አረጋግጠዋል።
በጥቃቱ ላይ የተሳተፉ ሁሉም ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ሥር ስለመዋላቸው የሚያጣራ የምርመራ ቡድን ተቋቁሞ እየተሠራ  እንደሆነና በውጤቱ መሠረትም ተጨማሪ ሰዎች በቁጥጥር ስዠሥር ሊውሉ እንደሚችሉ ተገምቷል።
 ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ጥቃቱን ተከትሎ ከሁለት ቀበሌዎች 200 የሚጠጉ ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው እንደሸሹና ለተፈናቃዮቹ የአካባቢው ነዋሪ እና መንግሥት ድጋፍ እያደረገላቸው መሆኑን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
 ጥቃቱን ፈርተው ቤታቸውን ዘግተው የሸሹ  የአንዳንድ ግለሰቦች ቤት ተሰብሮ ንብረታቸው እንደተዘረፈ ያስረዱት እኚህ የአካባቢው ነዋሪ፤ ከጥቃቱ ጋር በተያያዘም በቁጥጥር ሥር የዋሉ ግለሰቦች መኖራቸውን የሰሙ መሆኑን አስታውሰው፤ ኅብረተሰቡ ውስጥ ሆነው ታጣቂዎችን ሲረዱ የነበሩ ሰዎች አሁንም እንዳልተያዙና እንደተሰወሩ ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY