ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ኢትዮ ቴሌኮም በ2012 በጀት ዓመት 47 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ገቢ አግኝቻለሁ አለ።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ገቢው ከእቅዱ 105 ነጥብ 1 በመቶ ብልጫ እንዳለው ገልጸዋል።
ከመጠን በላይ የተጋነነ የጥሪና የመልእክት ክፍያ ያስከፍላል በሚል የሚተቸው ኢትዮ ቴሌኮም ያገኘው ገቢ፤
ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ፣ በ31 ነጥብ 4 በመቶ ብልጫ ያለው መሆኑን ያመላከቱት ሥራ አስፈጻሚዋ፤ ተቋሙ ከውጭ የስልክ ጥሪ 147 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘቱንም አስረድተዋል።
ከትርፍ ባሻገር ኩባንያው 10 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ብድር መመለስ እንደተቻለም በመግለጫው ላይ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ቁጥር ከባለፈው ዓመት አንጻር 5 ነጥብ 8 በመቶ አድጎ፣ 46 ነጥብ2 ሚሊየን እንደደረሰም ታውቋል።