የአማራ ክልል መንግሥት 1ሺኅ 244 ታራሚዎችን በይቅርታ ለቀቀ

የአማራ ክልል መንግሥት 1ሺኅ 244 ታራሚዎችን በይቅርታ ለቀቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአማራ ክልል መንግሥት በእስር ላይ የነበሩ 1 ሺኅ 244 የሕግ ታራሚዎችን በይቅርታ መልቀቁን የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ።

ከሐምሌ 21/2012 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑን ያስረዱት የዐቃቤ ሕጉ ሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ አቶ አለምሸት ምህረቴ፤ ይቅርታ የተደረላቸው በመደበኛው የይቅርታ አዋጅ ቁጥር 136/1998 መሰረት እና በልዩ ይቅርታ ቦርድ ጉዳያቸው ተጣርቶ የቀረቡ መሆናቸውን ይፋ አድርገዋል።
 ዕድሜያቸው የገፋ፣ የጤና ችግር ያለባቸው፣  በእድሉ ከተጠቀሙት መሀል አንድ ሦስተኛውን የእስር ጊዜያቸውን ያጠናቀቁና የባህሪ ለውጥ ያመጡ እንደሚገኙበት ያመላከተው መረጃ፤ በይቅርታ ከተለቀቁት ውስጥ 22 ሴቶች መሆናቸውን ያስረዳል።
በሙስና ፣ በጠለፋና አስገድዶ መድፈር ወንጀል የተፈረደባቸው በይቅርታው አለመካተታቸውን የገለጹት ሓላፊው፤ ይቅርታ የተደረገላቸው የሕግ ታራሚዎች ወደ ሕብረተሰቡ ሲቀላቀሉ የበደሉትን ሕዝብ በልማት ለመካስ ጠንክረው መሥራት እንዳለባቸውም ምክር ለግሰዋል።
በክልሉ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በመጋቢት ወር 2012 ዓ.ም መንግሥት በልዩ ሁኔታ ባደረገው ይቅርታ ከ7 ሺኅ የሚበልጡ የሕግ ታራሚዎች እንዲለቀቁ ማድረጉ የሚዘነጋ አይደለም።

LEAVE A REPLY