የጋምቤላ ክልል 3 ቢሊዮን 377 ሚሊዮን ብር በጀት ማፅደቁ ተሰማ

የጋምቤላ ክልል 3 ቢሊዮን 377 ሚሊዮን ብር በጀት ማፅደቁ ተሰማ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት በ5ኛ የምርጫ ጊዜ 5ኛ የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ጉባኤው የክልሉን የ2013 ዓመታዊ በጀት እና የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን ከማፅደቅ ባሻገር ሹመቶችን መስጠቱ ተሰማ።

ምክር ቤቱ በጉባዔው የ2012 የክልሉን መንግሥት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በመመልከት ያፀደቀ ሲሆን፤ የክልሉን ዋና ኦዲት መሥሪያ ቤት የ2012 በጀት ዓመት የኦዲት ሪፖርት እንደተመለከተ ተገልጿል።
የክልሉን ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዓመታዊ ሪፖርቱን ለምክር ቤቱ  ያቀረበ ሲሆን፤ በጉባዔውም የ5 ካቢኔ አስፈፃሚ አካላት ሹመት ለምክር ቤቱ ቀርቦ በሙሉ ድምፅ እንዲፀድቅ ተደርጓል።
ምክር ቤቱ ከወረዳ እስከ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ21 ዳኞች ሹመትን ሲያፀድቅ 2 ዳኞችን በሥነምግባር ምክንያት ማንሳቱ ታውቋል።
የጋምቤላ ግብርና ምርምር ማቋቋሚያ አዋጅ፣ በሕብረተሰቡ ተሳትፎ የለሙና ወደፊት እንዲለሙ የታሰቡ ተፋሰሶች መወሰኛ ረቂቅ አዋጅ፣ የክልሉ ሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅንና ሌሎችንም መርምሮ ማፅደቁ ይፋ ተደርጓል።
ምክር ቤቱ በጉባዔው የክልሉን የ2013 በ ዓመታዊ በጀት 3 ቢሊየን 377 ሚሊየን 653 ሺኅ 415 ብር እንዲሆን መደረጉ የተነገረ ሲሆን፤  ከክልሉ ዓመታዊ በጀት 2.3 ቢሊየን ብሩ ከፌዴራል መንግሥት በሚገኝ ድጎማ፣ ቀሪው በክልሉ የውስጥ ገቢ እንደሚሸፈን ታውቋል።

LEAVE A REPLY