ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ባለፉት 24 ሰዐታት በተደረገ 9 ሺኀ 786 የላብራቶሪ ምርመራ፤ 805 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር ገለጸ።
በድምሩ እስካሁን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 16 ሺኅ 615 መድረሱን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ይፋ አድርገዋል።
በተያያዘ ዜና ዛሬ የ10 ሰዎች ሕይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ መሆኑን ያመላከተው መግለጫ፤ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 263 እንደደረሰም አረጋግጧል።
በአንጻሩ ትናንት 78 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፤ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 6 ሺኅ 673 ደርሷል።
የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ መገኘቱ ከታወቀበት ከመጋቢት ወር ጀምሮ እስካሁን 413 ሺኅ 397 ሰዎች ምርመራ ተደርጎላቸው፣ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 16 ሺኅ 615 እንደደረሰ እለታዊው መግለጫ ያሳያል።
አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 9 ሺህ 587 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 134 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
እስካሁን በኢትዮጵያ 6 ሺኅ 763 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገገሙ፤ የ263 ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ 2 ሰዎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል።