በትግራይ ለምርጫ የተመዘገቡት አምስት ፓርቲዎች ከዛሬ ጀምሮ በፖሊሲዎቻቸው ላይ ይከራከራሉ ተባለ

በትግራይ ለምርጫ የተመዘገቡት አምስት ፓርቲዎች ከዛሬ ጀምሮ በፖሊሲዎቻቸው ላይ ይከራከራሉ ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኮሚሽን እውቅና ውጪ በ የተቋቋመው የትግራይ ክልል ምርጫ አስፈጻሚ ኮሚሽን በቀጣዮ ወር ለሚካሄደው ምርጫ አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች መመዝገባቸውን ገለጸ።

በምርጫው መሳተፍ የሚፈልጉ ፓርቲዎችና ግለሰቦች ከሐምሌ 21/2012 እስከ ሐምሌ 23/2012 እንዲመዘገቡ ቅዳሜ እለት  ባቀረበው ጥሪ መሰረት ግለሰቦችና የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደተመዘገቡ ኮሚሽኑ አስታውቋል።
በህወሓት ቀጥተኛ ትእዛዝና ምልመላ የተቋቋመው ምርጫ አስፈጻሚ እንደገለጸው ከሆነ ህወሓት፣ ባየቶና፣ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፣ የትግራይ ነጻነት ድርጅትና አሲምባ ዲሞክራሲያዊ ድርጅቶች በምርጫው ለመሳተፍ ፍላጎት አለን በሚል የተመዘገቡ ናቸው።
ከህወሓት ቀለብ ይሰፈርለታል በሚል የሚብጠለጠለው  “ባይቶና ” የተሰኘው ፓርቲ ፤ “ከፌደራል መንግሥት የሚመጣ ጫናን እንዲሁም በትግራይ ክልል መንግሥት አማካይነት እየተደረገ ያለውን አፈና ተቋቁመን ምርጫው ላይ ለመሳተፍ ወስነናል” በማለት ራሱን ገለልተኛና የትግራይ ሕዝብ ተቆርቋሪ አድርጎ ለማቅረብ የሞከረ ቢሆንም፣ “ሕግ ይከበር” የሚለውን ፌደራል መንግሥቱን እንደ ችግር ፈጣሪ የፈረጀበት አስተያየት ፓርቲው የህወሓት አሽከር መሆኑን በተግባር አረጋግጧል።
 የክልሉን የምርጫ ኮሚሽን የሚመሩት ኮሚሽነር ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም ፤ የመራጮች ምዝገባ እና ምርጫ የሚደረግበት ዕለት ውሳኔ በማግኘቱ  በቅርቡ ይፋ እናደርጋለን ብለዋል።
“ከዛሬ ጀምሮ ለምርጫ የሚወዳደሩ ፓርቲዎች የጊዜ ሰሌዳ ወጥቶላቸው በፖሊሲያቸው ላይ ክርክር ያደርጋሉ”  ያሉት ኮሚሽነሩ፤ ከምርጫው ጋር በተያያዘ ኮሚሽኑ በርካታ የሚጠበቁበትን ሥራዎችን ለማከናወን ዝግጁ ነው ብለዋል።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሰኔ ወር ባካሄደው ስብሰባ፤ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ውሳኔ ቢያሳልፍም፤ የትግራይ ክልል ምክር ቤት በበኩሉ ሰኔ 5/2012 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ በክልሉ ምርጫ እንዲካሄድ በሙሉ ድምጽ ውሳኔ ከማሳለፉ ባሻገር፣ በሰኔ ወር መጨረሻ ላይ የክልሉን የምርጫ ኮሚሽን ማቋቋሚያ፣ የምርጫ እና የምርጫ ሥነ ምግባር አዋጆችን ማፅደቁ አይዘነጋም።

LEAVE A REPLY