የፌዴሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል መንግሥት (ህወሓትን) አስጠነቀቀ

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል መንግሥት (ህወሓትን) አስጠነቀቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በሕገ ወጥ መንገድ እየተንቀሳቀሰ ነው በሚል እየተከሰሰ የሚገኘው የትግራይ ክልል መንግሥትን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስጠነቀቀ።

ህወሓት (የትግራይ ክልል መንግሥት) ምርጫ ለማካሄድ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በአፋጣኝ እንዲያቆም ነው ምክርቤቱ ኮስተር ያለ ማሳሰቢያ የሰጠው።
ክልሉ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ በሚጥል ድርጊቱ የሚቀጥል ከሆነ፤ ምክር ቤቱ በሕገ መንግሥቱ እና ሌሎች ሕጎች የተሰጠውን ሥልጣን ለመተግበር እገደዳለሁ ብሏል።
ይህን ዓይነት መልእክት ያዘለ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ለትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት ባለፈው ረቡዕ እንዲደርሰው መደረጉ ታውቋል።
  “የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥትና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ እንዲከበር ስለማሳሰብ” በሚል ርዕስ የተጻፈው ባለሦስት ገጽ ደብዳቤ፤ በቅርቡጨየፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ሆነው የተሾሙት የ አቶ አደም ፋራህ ፊርማ የሰፈረበት መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።
ምክር ቤቱ የሕገ መንግሥቱ ጠባቂ የበላይ ጠባቂ መሆኑን ያረጋገጠው ደብዳቤ፤ የትግራይ ክልል መንግሥት ወይም ህወሓት የራሱን የምርጫ ኮሚሽን በማቋቋም ጭምር እያካሄደው ያለው እንቅስቃሴ ግልጽ የሆነ የሕገ መንግሥት ጥሰት ነው ሲል ተችቶታል።
ምክር ቤቱ ተጣሱ ያላቸውን የሕገ መንግሥት አንቀጾች በደብዳቤው በዝርዝር ካሰፈረ በኋላ ፤ እንዲህ ዓይነቱ ሕግን የሚጻረር ምርጫ የትግራይ ክልላዊ መንግሥት በፍጥነት እንዲያቆም አሳስቧል።

LEAVE A REPLY