በዐሥር ዓመት ውስጥ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚያገናኙ ጠቅላላ መንገዶች ይገነባሉ ተባለ

በዐሥር ዓመት ውስጥ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚያገናኙ ጠቅላላ መንገዶች ይገነባሉ ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በኢትዮጵያ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት  ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚያገናኙ ጠቅላላ መንገዶችን ግንባታ ለማከናወን እቅድ መያዙን የፌዴራል መንገዶች ባለሥልጣን ገለጸ።

ተቋሙ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በ10 ዓመቱ መሪ የልማት እቅድ ላይ እየተወያየ በሚገኘበት መድረክ ላይ እቅዱን በማቅረብ ጥልቅ ውይይት አካሂዷል።
ዛሬ የተጀመረውና ለሦስት ቀናት በሚቆየው ውይይት ላይ የ10ሩ ተጠሪ ተቋማት እቅድ የቀረበ ሲሆን፤ የመሪ ልማት እቅዱ ውይይት በተጀመረበት በዛሬው እለት የፌደራል መንገዶች ባለሥልጣን በሀገሪቱ ባሉ ሁሉም ወረዳዎች የአስፋልት መንገድን ለመሥራት፤ እንዲሁም ወደ ጎረቤት ሀገራት ከተሞች የሚደረግን ጉዞ የሚያቀላጥፍ 21 መንገድ ግንባታ ለማከናወን ማቀዱን ይፋ አድርጓል።
በታቀደው ፕሮግራምና በዘርፉ ከ3 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ዜጎች የሥራ እድል ይፈጠራል የሚል መግለጫም ከመድረኩ ተሰምቷል።
 የመንገድ ግንባታው ለኢኮኖሚው ትልቅ ድርሻ ያላቸውን የግብርና፣ የነዳጅ፣ የቱሪዝም እና የኢንዱስትሪ ዘርፎች የሚደግፍ ከመሆኑ አኳያ ለሥራው ከፍተኛ ትኩረት ይሰጠዋል ተብሏል።

LEAVE A REPLY