ከነሀሴ ወር የመጨረሻ ሳምንት በፊት ማንኛውም ት/ቤት ምዝገባ እንዳያደርግ መንግሥት አስጠነቀቀ

ከነሀሴ ወር የመጨረሻ ሳምንት በፊት ማንኛውም ት/ቤት ምዝገባ እንዳያደርግ መንግሥት አስጠነቀቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና–  ከነሀሴ ወር የመጨረሻ ሳምንት አስቀድሞ ምንም ዓይነት የቀጣይ ዓመት የትምህርት ምዝገባ ማከናወን እንደማይቻል ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።

አሁን ላይ አንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ወላጆችን እያስገደዱ ምዝገባ በማካሄድ ላይ መሆናቸውን የጠቆመው ትምህርት ሚኒስቴር፤ ማንኛውም ትምህርት ቤት ከነሀሴ ወር የመጨረሻው ሳምንት በፊት የትኛውንም ዓይነት ምዝገባ ማከናወን አይፈቀድም ብሏል።
 የትምህርት ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ጉዳዬች ዳይሬክተር ወይዘሮ ሐረጓ ማሞ ፤ ይህንን የመንግሥት መመሪያ ተላልፈው ምዝገባ በሚያከናውኑ ትምህርት ቤቶች ላይ አስፈላጊው የእርምትና የሕግ እርምጃ እንደሚወሰድ አሳስበዋል።
የተማሪዎች የቀጣይ ዘመን ምዝገባ የግዜ ሰሌዳ እንዲራዘም የተፈለገው የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት መስፋፋትን ተከትሎ ወላጆች እና ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት የሚያደርጉትን ጉዞ በመግታት፣ የቫይረሱን ስርጭት ለመቀነስ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል።
ወላጆች መንግሥት ትምህርት እንዲጀመር ሲያሳውቅ ብቻ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን ተገንዝበው ፣ ልጆቻቸው በእጃቸው ላይ የሚገኙትን የመማሪያ ቁሳቁሶች እንዲያጠኑ ድጋፍ እንዲያደርጉም ሚኒስቴሩ ዛሬ መልእክት አስተላልፏል።

LEAVE A REPLY