ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ዱባይ (የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች) የአረቡ ዓለም የመጀመሪያ የሆነው የኒውክሌር ማብለያ ጣቢያ ሥራ ማስጀመሯ ተነገረ።
በጎርጎሳዉያኑ የቀን ቀመር 2017 ላይ ሊጀመር እቅድ ተይዞለት የነበረው የኒውክሌር ጣቢያ ከሦስት ዓመታት መዘግየት በኋላ፣ የደቡብ ኮሪያ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ወደ ሥራ መገባቱ ተረጋግጧል።
“ባራካሃ” የተሰኘው ይህ የኒውክሌር ጣቢያው በነዳጅ ሀብቷ ኢኮኖሚዋ በከፍተኛ ሁኔቴ ለፈረጠመው የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ተጨማሪ የገቢ አማራጭ እንደሚሆናት እየተነገረ ነው።
ዱባይ ከሁለት ሳምንታት በፊት ወደ ማርስ በማቅናት ከባህረ ሰላጤው አገራት በህዋ ምርመራ ፈር ቀዳጅ ለመሆን ከመቻሏ ባሻገር፤ ከፀሐይ ብርሃን ኃይል ለማመንጨት ከፍተኛ ገንዘብ መድባ እየሠራች መሆኗን መረጃዎች ይጠቁማሉ።
አብዛኞች የባርካሀ ኒውክለር ማብለያ ጣቢያ አስፈላጊነት ላይ ጥያቄያቸውን እያነሱ ሲሆን፤ ይህን የኒውክለር ጣቢያ ለመመስረት፣ ለማንቀሳቀስ እና የሚያስገኘውን ጥቅም ከፀሐይ ብርሃን ኃይል ጋር በማነጻጸር የኒውክሌር ማብላያ ጣቢያ ፕሮጀክቱን ሲያጣጥሉት ታይተዋል።
በቀጠናው የተባበሩት አረብ ኢምሬቶችና የሳዑዲ አረቢያ ዋነኛ ተቀናቃኝ የሆነችው ኳታር፤ “ባራካሃ ” የሚል ስያሜ የተሰጠው የኒውክሊየር ጣቢያ ለቀጠናው ሰለም፣ ደህንነት እና አየር ስጋት ነው በሚል ስትቃወም መቆየቷ ይታወሳል።
ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ የኒውክሊየር ማብላያ ጣቢያውን እየገነባች ያለችው ከኳታር ድንበር አቅራቢያ ላይ ሲሆን፤ ሌላኛዋ ከባህራ ሰላጤ አገራት በቅርበ ርቀት ላይ የምትገኘው ደግሞ ኢራን ነች። ኢራን በኒውክለር ማብለያ ጣቢያዋ ምክንያት በአሜሪካ ማዕቀብ ከተጣለባት ሰንበትበት ብሏል።
የኒውክለር አማካሪ ቡድን ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ዶ/ር ፖል ዶርፍማን ፤ ከአንድ ዓመት በፊት ኒውክለር ማብላያ ጣቢያ በባህረ ሰላጤው አገራት መካከል የሚኖረውን ፖለቲከዊ ግነኙነት ከባድ እንደሚያደርገውና አዲስ የኒውክለር ማብላያ ጣቢያ ፣ የኒውክለር ጦር መሳሪያ ባለቤት ማድረግ እንደሚችል የሚያሳይ ጽሑፍ አቅርበው ነበር።
ይህ ሰሞነኛው የዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ ፕሮጀክት በባህረ ሰላጤው ሀገራት የሬዲዮ አክቲቭ ብክለት ሊያስከትል እንደሚችል እየተነገረ ቢሆንም፤ የዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ የኒውክር ኢነርጂ ቴክኖሎጂ ኮርፖሬሽን ባወጣው መግለጫ እየቀረበ ያለውን ክስና ወቀሳ አጣጥሏል።