42 ሺኅ ዜጎቿ በኮሮና ቫይረስ የሞቱባት ኢራን 12 ሺኅ ብቻ አድርጋ ማቅረቧ...

42 ሺኅ ዜጎቿ በኮሮና ቫይረስ የሞቱባት ኢራን 12 ሺኅ ብቻ አድርጋ ማቅረቧ በምርመራ ተጋለጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ኢራን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር መንግሥት በይፋ ከገለጸው በሦስት እጥፋ እንደሚበልጥ የቢቢሲ ፐርሺያ ምርመራ ይፋ አደረገ።

ለሕዝብ ይፋ ያልሆነ የኢራን መንግሥት አኃዝ በኮቪድ-19 ምክንያት ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር  42ሺህ የሚጠጋ ቢሆንም፤ የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር  ግን እስካሁን በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 14ሺህ 405 ነው ሲል በጣም ዝቅተኛ ቁጥር ጠቅሷል።
ከኢራን መንግሥት የተገኘው መረጃ በተጨማሪም በቫይረሱ ስለመያዛቸው በይፋ የተነገረው ቁጥር በግማሽ እንዲቀንስ መደረጉን ያሳያል።
የሀገሪቱ ጤና ሚንስቴር እስካሁን በቫይረሱ ተይዘዋል ያላቸው ሰዎች ቁጥር 278 ሺኅ 827 ቢሆንም፣ ይሁን እንጂ የሀገሪቱ መንግሥት 451ሺኅ 024 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውን ገልጿል።
የኢራን መንግሥት በቫይረሱ የተያዙ እና የሞቱ ሰዎች ቁጥርን ከማሳነሱም ሌላ በቫይረሱ ሳቢያ ህይወታቸው ማለፍ ከጀመረ ከአንድ ወር በኋላ ነበር፣ የሀገሪቱ የጤና ሚንስቴር በቫይረሱ ሳቢያ የሰው ህይወት ማለፉን ሪፖርት ማድረግ የጀመረው።
በተጋለጠው ሪፖርት መሠረት መንግሥት የመጀመሪያውን ሟች ይፋ በሚያደርግበት ወቅት 52 ሰዎች ቀድመው በኮቪድ-19 ምክንያት ህይወታቸውን አጥተው ነበር።
ማንነቱ ይፋ ያልሆነው ምንጭ ለቢቢሲ የላከው መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነ በመላው ኢራን በየዕለቱ በኮቪድ-19 ተይዘው ወደ ሆስፒታል የሚገቡ ሰዎችን ዝርዝር መረጃ የያዘ ነው። ሥም፣ እድሜ፣ ጾታ፣ ታማሚው የሚታይበት ምልክት፣ ቀን እና ተጠቂው የተጓዳኝ በሽታ ታማሚ ስለመሆኑ እና ሌሎች መረጃዎችም ተካተውበታል።

LEAVE A REPLY