ሒሩት ክፍሌ በ6 ሺኅ ብር ዋስትና እንድትፈታ ተወሰነ

ሒሩት ክፍሌ በ6 ሺኅ ብር ዋስትና እንድትፈታ ተወሰነ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በድምጻዊ ሀጫሉ ግድያ ከተነሳው ኹከት ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባን ወጣቶች አደራጅተሻል በሚል የተከሰሰችው ሒሩት ክፍሌ በዋስ ተለቀቀች።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የፓርቲው ማኅባራት ተጠሪ፤ ሒሩት ክፍሌ በስድስት ሽሕ ብር ዋስ ለእስር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት የወሰነው ዛሬ ነው።
ቀደም ባለው የወያኔ / ኢሕአዴግ ዘመን ለሠባት ጊዜያት ያህል ታስራ የነበረችው ሒሩት ክፍሌ፤ ሰኔ 23/2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ የተከሰተውን ግርግር አደራጅተሻል በሚል ፖሊስ ጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ያዋላት ከሦስት ሳምንት በፊት ነበር።
በዚህ መሠረት ጉዳዮ በፍርድ ቤት ሲታይ ቆይቶ ዛሬ ሐምሌ 28/2012 በቀጠሮዋ ችሎት የቀረበችው ሒሩት ክፍሌ በስድስት ሽኅ ብር ዋስ እንድትለቀቅ ፍርድ ቤት ወስኗል።
የፌደራል ፖሊስ መርማሪ ቡድን  ምርመራዬን አልጨረስኩም በሚል ተጨማሪ ጊዜ ቢጠይቅም ችሎቱ ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ የተጠርጣሪ የዋስ መብት እንዲጠበቅ አዝዟል።

LEAVE A REPLY