በሊባኖስ 5 ኢትዮጵያውያን እንደተጎዱና በርካቶች የደረሰቡት እንደጠፋ ተሰማ

በሊባኖስ 5 ኢትዮጵያውያን እንደተጎዱና በርካቶች የደረሰቡት እንደጠፋ ተሰማ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በሊባኖስ፣ ቤይሩት ትናንት በደረሰው ፍንዳታ ከፍተኛ ጉዳት  ካጋጠማቸው መሀል ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙበት ተሰማ።

በቤይሩት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን በማናገር መረጃውን ያሰራጨው ቢቢሲ በዚህ ከባድ ፍንዳታ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ ጉዳት መድረሱን ጠቁሟል።
 ኢትዮጵያዊያኑ ስላሉበት ሁኔታ በቅርብ እየተከታተልኩ ነው ያለው በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጀነራል የሆኑት ተመስገን ኡመር ፤ የደረሰው ፍንዳት ከባድ ከመሆኑ አንጻር በከተማዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊን ላይም ጉዳት እንደደረሰ ጥቆማ ደርሶናል ብለዋል።
 አምስት ያህል ኢትዮጵያዊያን መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል መግባታቸውን መነገሩን ተከትሎ የመረጃውን ትክክለኛነት ለማጣራትና ያሉበትን ለማወቅ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ሓላፊው ተናግረዋል።
 ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ኢትዮጵያዊያን የሕክምና እርዳታ አግኝተው ወዲያ ወደ ቤታቸው መመለሳቸውንና በከተማዋ ውስጥ ባለው ሁኔታ ምክንያት ተገቢውን መረጃ በፍጥነት ማግኘት እንዳልተቻለም ታውቋል።
  ከፍንዳታው በኋላ የቆንስላው ሓላፊና ሠራተኞች የኢትዮጵያዊያኑን ሁኔታ ለማወቅ ሌሊቱን ወደ ተለያዩ አካባቢዎችን የሕክምና ቦታዎች በመሄድ ሲያጣሩ እንደነበር በቤይሩት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለቢቢሲ ገልጸዋል።
በቤይሩት፣ ሊባኖስ የኢትዮጵያዊየን በጎ አድራጎት ማኅበር ከሆነው “የእኛለኛ በስደት” አባላት ለቢቢሲ የተሰጠው መረጃ እንደሚያሳየው፤ ባጋጠመው ፍንዳታ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ኢትዮጵያዊያን ቀላልና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑንና ቁጥራቸው ያልታወቀ ደግሞ የት እንዳሉ ማግኘት እንዳልተቻለ ያረጋግጣል።
እስካሁን በተሰበሰበው መረጃ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ጥቂት ሲሆኑ፣ አብዛኞቹ ግን ቀላል የሚባል ጉዳት አጋጥሟቸው ትናንት ከፍንዳታው በኋላ አንስቶ እስከጨዛሬ ድረስ ወደ ሕክምና መስጫ ተቋማት በመሄድ ድጋፍ አግኝተው ወደ መኖሪያቸው መመለሳቸው ታውቋል።
የማኅበሩ አባላት አለን ባሉት መረጃ መሰረት ሁለት ኢትዮጵያዊያን ላይ ጉዳት ደርሶ ሆስፒታል መግባታቸውንና አንዲት ኢትዮጵያዊት ያለችበትን ለማወቅ ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ፣ እንዲሁም አንዳንድ ኢትዮጵያዊያን ማግኘት ስላልቻሏቸው ጓደኞቻቸው በተደጋጋሚ እየጠየቁ መሆናቸውን ይፋ አድርገዋል።

LEAVE A REPLY