በኮሮና ቫይረስ 13 ሰዎች ሲሞቱ 459 ሰዎች በኮቪድ 19 ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ

በኮሮና ቫይረስ 13 ሰዎች ሲሞቱ 459 ሰዎች በኮቪድ 19 ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ባለፉት 24 ሰዐታት ለ7 ሺኅ 319 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 459 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ፣ የ13 ሰዎች ሕይወት በቫይረሱ ምክንያት ማለፉ ተነገረ።

የዛሬውን የሞት ምዝገባ ተከትሎ በኢትዮጵያ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 356 መድረሱን የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።
በአንጻሩ በትናንትናው ዕለት 358 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ከመሆኑ አኳያ ከበሽታው ያገገሙሙ ሰዎችን ቁጥር 8598 አድርሶታል፡፡
ባለፈው መጋቢት ወር መጀመሪያ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙት ሰዎች ቁጥር ከሀያ ሺኅ ማለፉም ታውቋል።

LEAVE A REPLY