ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በተለያዩ አካባቢዎች የሚታየውን ጽንፈኝነት በማክሸፍ አገራዊ ሰላምና አንድነት ላይ የሃይማኖት ተቋማትና መሪዎቻቸው እንዲሠሩ ጥሪ ቀረበ።
የሰላም ሚኒስትሯ ሙፈሪያት ካሚል በ12ኛው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር በዚህ ወቅት ሃይማኖትን ሽፋን ያደረጉ፣ ነገር ግን ከሃይማኖት መሠረታዊ መርህዎች ጋር ተቃራኒ የሆኑ ተግባራት በኢትዮጵያ እየተስተዋሉ መሆኑን ገልጸዋል።
ከዚህ አኳያ የሃይማኖት ተቋማት፣ መሪዎች፣ እንዲሁም አስተማሪዎች ሁኔታውን አክሽፈው ሰላምና አንድነት እንዲጠነክር የጋራ የሆኑ የሃይማኖት እሴቶችን መሰረት በማድረግ ሀገራዊና ሃይማኖታዊ ሓላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።
በተያያዘ ዜና የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በምዕራብ አርሲ ዞን በመገኘት ባለፈው ወር በፀጥታ ችግር ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ቤተሰቦችን የጎበኙ ሲሆን፣
የሀገር ሽማግሌዎቹ በአጠቃላይ በ25 ከተሞች የደረሰውን ጉዳት ተዘዋውረው ከመመልከታቸው ባሻገር ፤ መንግሥት የሀገርን ሰላም ለማስከበርና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ መሥራት እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል።