በቤይሩቱ ፍንዳታ አንድ ኢትዮጵያዊ ሲሞት፣ ዐሥር ሰዎች ሆስፒታል መተኛታቸው ተረጋገጠ

በቤይሩቱ ፍንዳታ አንድ ኢትዮጵያዊ ሲሞት፣ ዐሥር ሰዎች ሆስፒታል መተኛታቸው ተረጋገጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና–  በቤይሩት  ከትናንት በስቲያ በደረሰው ከባድ ፍንዳታ አንድ ኢትዮጵያዊ ሕይወቱ ማለፉ ታወቀ።

በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄነራል የሆኑት አቶ ተመስገን ኡመር በአደጋው አንድ ኢትዮጵያዊ መሞቱንና ከዚህ በተጨማሪ አንዲት በፍንዳታው ጉዳት የደረሰባት ሴት ሕክምና እየተከታተለች የነበረች ኢትዮጵያዊት በጽኑ ህሙማን ማቆያ ውስጥ እንደምትገኝም አረጋግጠዋል።
ከሁለት ቀን በፊት በተከሰተው ዘግናኝ አደጋ ዐሥር ኢትዮጵያዊያን ጉዳት እንደደረሰባቸው ቆንስላው በትናንትናው ዕለት ማስታወቁ አይዘነጋም።
በከተማዋ ያሉ ኢትዮጵያዊያን ስላሉበት ሁኔታ በቅርብ እየተከታተለ ያለው በቤይሩት የኢትዮጵያ ቆንስላ ፤ የደረሰው ፍንዳታ ከባድ ከመሆኑ አንጻር በከተማዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊን ላይም ጉዳት መድረሱን ከመግለጹ ባሻገር፣ ከተጎጂዎቹ መካከል ሁለቱ መካከለኛ፣ ሠባቱ ደግሞ ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው (አንድ ግለሰብ መሞቱን ጨምሮ)  ይፋ ቢያደርግም በመንግሥት በኩል እስካሁን የተነገረ ይፋዊ መግለጫ የለም።

LEAVE A REPLY