ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በ2012 ዓመት የምርት ዘመን በዓይነቱ ልዩ የሆነ የፈሳሽ ማዳበሪያ በኢትዮጵያ መከፋፈሉን ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን አስታወቀ።
በተወሰኑ አካባቢዎች የመሬቱ እና አፈሩ ዓይነት እየተጠና ጥቅም ላይ እንዲውሉ ይደረጉ የነበሩና በአንጻሩም በኹሉም ስፍራዎች ጥቅም ላይ እንዲውሉ የማይደረጉ ማዳበሪያዎች ከዚህ ቀደም ወደ አገር ውስጥ ይገቡ ነበር። የፈሳሽ ማዳበሪያው ግን በሁሉም አካባቢዎች ተግባራዊ ቢደረግ ውጤታማ እንደሚሆን በመታመኑ መሆኑ ተጠቅሷል።
ከተለመደው የማዳበርያ አቅርቦት ጋር ተገናኝቶ አዳዲስ የግብርና ግብዓቶችን በማስተዋወቁ ረገድ በምርት ዓመቱ 15 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት የፈሳሽ ማዳበርያ እንደተሰራጨ ታውቋል።
የማዳበርያ ፍላጎቱ ከዚህ ቀደም ላቅ ባለ ሁኔታ መጨመሩን እና እንደውም የአዲሱ ፈሳሽ ማዳበርያ አይነት ፈላጊው በመብዛቱ እጥረት ያጋጠመ ሲሆን፣ እያደገ ከመጣው የማዳበሪያ ፍላጎት አንጻር በተገቢው ሁኔታ ማዳበሪያዎችን ማቅረብ እንዳልተቻለ፣ በተለይም ከውጭ ምንዛሪ ዕጥረት ጋር ተዳምሮ ችግሩን እንደሚያሰፋው ተነግሯል።
የፈሳሽ ማዳበሪያው በአርሶ አደሮች ዘንድ ተፈላጊነቱ በመጨመሩ እና እንደልብ ማቅረብ ሳይቻል በመቅረቱ ዕጥረቱ መባባሱን የተናገሩት የኮርፖሬሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ፤ በ2012/2013 የሰብል ምርት ዘመን 14.58 ሚሊዮን ኩንታል የሚሆን የተለያዩ አይነት የአፈር ማዳበርያ ግዢ መከናወኑንም ይፋ አድርገዋል።
ከተገዛው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 13.55 ሚሊዮን ኩንታል (92) በመቶውን ማሰራጨት መቻሉን በባለፈው በጀት ዓመት ሪፖርት ላይ የተጠቀሰ ሲሆን፣ ከተሰራጨው ማዳበርያ የቀረውን ደግሞ በአሁኑ ወቅት በምርት ዓመቱ የአሮጌ ኬሚካሎች እና መርጫ መሣሪያዎች አቅርቦት የብር 658.9 ሚሊዮን ግዢ ተፈፅሞ፤ ለክልሎች በግብርና ሚኒስቴር ድልደላ መሰረት በመከፋፈል ላይ እንደሚገኝ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2012 በጀት ዓመት ሪፖርቱ በግልጽ አስቀምጧል።