ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ መድረክ ከኦፌኮ ጋር እንደማይቀጥል አስታወቁ

ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ መድረክ ከኦፌኮ ጋር እንደማይቀጥል አስታወቁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ለበርካታ ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ሠፊ ተሳትፎ በማድረግ የታወቁት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በአክራሪ የኦሮሞ ብሔርተኝነት እንቅስቃሴ ውስጥ ከተዘፈቀው ኦፌኮ ጋር በርካታ ፓርቲዎችን ያቀፈው “መድረክ” መቀጠል እንደማይችል ተናገሩ።

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ  አንድነት መድረክ አባል ከሆኑት የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ  አንዱ ከሆነው፣ በመራራ ጉዲናና በቀለ ገርባ የሚመራው (በቅርቡ ጃዋር መሐመድ ተቀላቅሏቸዋል) ኦፌኮ (ኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ) ጋር ድርጅታቸው ኢሶዴፓን ጨምሮ የጋራ መድረኩ ለመቀጠል እንደሚከብደው ፕሮፌሰሩ አስረድተዋል።
ኦፌኮ በጃዋር መሐመድ አጋፋሪነት ለቀጣዮ ምርጫ ከኦነግና ከኦብፓ ጋር መጣመሩን ተከትሎ በመድረክ ውስጥ አባል የሆነ ፓርቲ ከሌላ ፓርቲ ጋር ጥምረት መፍጠር እንደማይችል ያስታወሱት ፕሮፌሰር በየነ፤ ጉዳዮን አስመልክቶ ለኦፌኮ አመራሮች በተደጋጋሚ ማብራሪያ እንዲሰጡ ቢነገራቸውም በዝምታ ማለፋቸውን ይፋ አድርገዋል።
የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራሲ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) ሊቀመንበር የሆኑት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፤ አሁን ኦፌኮ በግልፅ እያሳየ ባለው የአቋም ልዮነት የተነሳ  ከሌሎቹ ፓርቲዎች ጋር በመድረክ ውስጥ አባል ሆኖ መቀጠል የሚያስችለው እድል እንደሌለም ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY