565 ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ሲያዙ፣ 17 ሰዎች በቫይረሱ ለሞት ተዳርገዋል

565 ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ሲያዙ፣ 17 ሰዎች በቫይረሱ ለሞት ተዳርገዋል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በኢትዮጵያ ተጨማሪ 565 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ እንደተያዙና 17 ሰዎችም በበሽታው ለሞት እንደተዳረጉ ተሰማ።

ባለፉት 24 ሰዐታት ለ9 ሺኅ 035 ሰዎች በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ፣ 565 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡን የጤና ሚኒስትር አስታውቋል።

በተያያዘ ባለፋት 24 ሰዐታት የ17 ሰዎች ሕይወት በቫይረሱ መሞታቸውን ተከትሎ፣ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርን 407 አድርሶታል።
በአንጻሩ ትናንትና 499 ሰዎች ማገገማቸው የተነገረ ሲሆን፣ ይህም ከበሽታው ያገገሙ ሰዎችን ቁጥር 10 ሺኅ 206 እንዳደረሰው የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።
እስካሁን በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ድምርም 22 ሺኅ 818 መድረሱን ቢሮው ይፋ አድርጓል።

LEAVE A REPLY