በኦነግ ጽ/ቤት ትናንት ተሰጠ ስለተባለው መግለጫ እንደማያውቁ ዳውድ ኢብሳ ተናገሩ

በኦነግ ጽ/ቤት ትናንት ተሰጠ ስለተባለው መግለጫ እንደማያውቁ ዳውድ ኢብሳ ተናገሩ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀ መንበር ከፍተኛ አመራሮች ትናንት ሰኞ አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው የድርጅታቸው ጽ/ቤት ስለሰጡት መግለጫ የሚያውቁት ነገር አለመኖሩን ገለጹ።

“ስለ መግለጫው አላውቅም፤ አጀንዳውም፣ አላማውም ምን እንደሆነ አይገባኝም” ያሉት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ስለተከናወነው ነገር የሚያውቁት አለመኖሩን ከመግለጻቸው ባሻገር፤ በግንባሩ ስም በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ የሰጡት ከፍተኛ አመራሮች ም/ሊቀመንበሩ አቶ አራርሶ ቢቂላ፣ ቃል አቀባዮ አቶ ቶሌራ አደባ  እና አቶ ቀጀላ መርዳሳ የተባሉ ግለሰቦች በጋራ በመሆን ኦነግን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እንደሰጡም አብራርተዋል።
 ” ኦነግ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ቢወስንም አመራሮቹና አባላትን በማሰር፣ እንዲሁም ስሙን የማጠልሸት ዘመቻ እየተካሄደበት ነው” ሲሉ በመግለጫው የተናገሩት የኦነግ ሦስቱ አመራሮች፤ ከእነዚህ ችግሮች በተጨማሪ ኦነግ በመቶዎች የሚቆጠሩ አባላቱ ታስረውበታል ብለዋል።
ከአሥራ አምስት ቀን በፊት  ግንባሩን ለበርካታ ዓመታት በጫካ ቆይታውና በኤርትራ አክራሞቱ የመሩት አቶ ዳውድ ለደኅንነታቸው ሲባል በጸጥታ ኃይሎች ከቤታቸው እንዳይወጡ መዳረጋቸውን ተከትሎ፤ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በጽህፈት ቤቱ ስብሰባ ማካሄዳቸው ይታወሳል።
በወቅቱ ጉዳዮን የኦነግ የሕግና የቁጥጥር ኮሚቴ የማጣራት ሥራ እንደሚያደርግ ያስታወቁት አቶ ዳውድ ኢብሳ  ቀደም ያለው ስብሰባ ጉዳይ እስኪጣራ ድረስ መግለጫ መስጠት መከልከሉን፣ የትናንቱ ጋዜጣዊ መግለጫም ይህን የሚጣረስ እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
“የተከናወነው ስብሰባ በጣም የተምታታ ስለሆነ የሕግና የቁጥጥር ኮሚቴው እስከሚያጣራ ምንም አይነት መግለጫ እንዳይሰጥ ተብሎ አቁሟል። እነሱም ምን መግለጫ እንደሚሰጥ አናውቅም ብለው መልሰውልኛል። የማምታታት ሥራ እየተሠራ ነው” ያሉት ኦቦ ዳውድ ኢብሳ፤
አሁን ባለው የፖለቲካ ሁኔታ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ኢላማ ውስጥ ወድቋል ሲሉም ገልጸዋል።
“መንግሥት በራሱ የዴሞክራሲ ሂደት፣ በሰላም መንቀሳቀስ ሲያቅተውና ተፎካካሪ ፓርቲ ሲበረታበ፤ በገንዘብም ይሁን በማስፈራራት በፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ ጣልቃ ይገባል” በማለት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት በኦነግ ውስጥ መከፋፋል እንደፈጠረ የጠቆሙት የግንባሩ ሊቀመንበር፤  ቀደምሲልም መሰል ጣልቃ ገብነት በግንባራቸው ላይ ሲሞከር እንደነበረ አብራርተዋል።

LEAVE A REPLY