ብልፅግና ፓርቲ አሻጋሪ ወይስ የዘር ፍጅት (Genocide) መርዶ ነጋሪ? || ከሸግየ ነብሮ...

ብልፅግና ፓርቲ አሻጋሪ ወይስ የዘር ፍጅት (Genocide) መርዶ ነጋሪ? || ከሸግየ ነብሮ ​​​​​​​​​ኢጆሌ ባሌ

ብልፅግና ፓርቲ ሀገር በሕግና ሥርዓት እየመራ ወደ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት አሻጋሪ ወይስ የዘር ፍጅት (Genocide) መርዶ ነጋሪ?

“If you do not fight at least have the decency to respect those who do.

Jose Marti

ከግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ወዲህ ኢትዮጵያን እናስተዳድራለን ብለው የመጡት ሁሉ ሀገሪቱን ቤተሙከራ ወይም ላባራቶሪ አድርገዋታል።

ደርግ የባለ ብዙ ወግ ባህልና ሀይማኖት ባለቤት የሆነችውን ታላቅ ሀገር የዘመኑን ነፋስ ተከትሎ በአንድ ጀምበር ሶሻሊስት አደርጋታለሁ ብሎ ሲባዝን ሀገሪቷን አደህይ የተቃወሙትን ሁሉ አጥፍቶ ምሑራኖቿን ሰውቶ የጦር አውድማ ካደረጋት በኋላ ለጎጠኛ ዘረኛ ዘራፊዎች ሰጥቶን እስከውዲያኛው አሸልቧል።

 “የታደለች ቅማል ተጉዛ ተጉዛ፣

ቤተመንግሥት ገባች ሕወሓትን ይዛ”

የሽፍታው የወያኔ መንግሥት ለዝንተ ዓለም በስልጣን ላይ ተቀምጨ ለመዝረፍ ይጠቅመኛል በሚል ሀገሪቱን በዘርበሀይማኖት በመከፋፈል የጎሣ ፌደራሊዝም ዘርግቶ በልማታዊ መንግሥት ስም እራሱንና ጭፍሮቹን ሲያለማ፣ የተቃወሙትን ሁሉ ሲያሰቃይና በጥይት ሲቆላ ከከረመ በኋላ በዱባይ፣ በአውሮፓና አሜሪካ ንብረት አፍርቶ በአዲስ አበባ በዘመድ አዝማዶቹ ስም እየገደና ህንፃ እያከራየ መቀሌ ላይ በድሎት እየተንፈላሰሰ ሀገር በማተራመስ ላይ ይገኛል።

ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ የወያኔ ማፊያ ቡድን የግፍ አገዛዝ አንገሽግሾት ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሎ ያነሳውን አመፅ (ፅንፈኞች የእነርሱ ብሔር ትግል ውጤት ብቻ ሊያደርጉት ይሞክራሉ) ተከትሎ የኢትዮጵያን ስም ከፍ አድርጎ በማጮህ ያማለለውን የቲም ለማን ቡድን ሆ ብሎ ተቀብሎ በስልጣን ላይ እንዲቀመጥ ፈቅዶለታል። በዶ/ር አብይ የሚመራው መንግሥት በዘመናዊ አስተዳደር የሀገሪቱን ሉዐላዊነት ፀጥታና ሰላም አስከብሮ የሕዝቧን የደህንነት ዋስትና አስጠብቆ በሕግ ይመራታል ተብሎ ሲጠበቅ አዲስ መርህ አውጥቶ ፅንፈኛ፣ ዘራፊ ጅብና ሰፊውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አዋህጄ በመደመር ፍልስፍና ኢትዮጵያን እመራለሁ ብሎ በመነሳት ሀገቱን ለብጥብጥና ለመከፋፈል፣ ሕዝቧን ከሰብዓዊነት ውጪ በኢንተርሃሞዌዎች እንዲጨፈጨፍና ንብረቱም ዶግ አመድ እንዲሆን አድርጎታል። በስልጣን ላይ ያለው መንግሥት በእኩልነት መርህ ዴሞክራሲን በማስፈን እስከ ቀጣዩ የሕዝብ ምርጫ ያስተዳድራል ተብሎ ቢጠበቅም በድክመት ላይ ድክመት እያሳየ ሀገሪቱ በሌላ ብጥብጥና አመፅ ስሟ እንዲነሣ በማድረግ ላይ ይገኛል።

ሕዝቡ ጥርሱን የነከሰባቸው የቀድሞ መንግሥት ባለስልጣናት አሁንም በሹመኝነትና በዲፕሎማትነት ተሹመዋል። (በጉራ ፈርዳ የአማራውን ብሔረሰብ አፈናቅሎ ሜዳ ላይ የበተነው ሺፈራው ሺጉጤ፣ በደቡብ ጎንደር ሕዝብን በግፍ የጨፈጨፈው ካሣ ተክለብርሃን፣ የአቃቤ ሕግ ሹም ሆኖ ፖለቲከኞችን በሀሰት እየከሰሰና እያስመሰከረ ሲያሰቃይ የነበረው ብርሃኑ ፀጋየ ከሚጠቀሱት ጥቂቶቹ ናቸው።) ቁልፍ የመንግሥት የስልጣን ቦታዎችን ለአንድ ብሔር በመስጠት ተረኝነት በጉልህ እንዲታይ ተደርጓል።

ለተረኛው ብሔር ፅንፈኞች መረን የለሽ ነፃነት በመስጠትወጣቱን በመመረዝ ንፁሓን በተደጋጋሚ ተጨፍጭፈዋል፤ የሀገሪቱ ሀብትም በከፍተኛ ደረጃ ወድሟል። ሁሉን የኔ (ኬኛ) የሚል መንጋ ተፈጥሮ ሀገር ከማተራመስ አልፎ ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጎን በመሰለፍ Down, Down Ethiopia እስከማለት ተደርሷል። ጥቂት የተማርን ነን ባይ ፅንፈኞች መቀሌ እየተመላለሱ መመሪያ ተቀብሎ በመምጣት የወያኔን ተልዕኮ ለማስፈፀም ሲሯሯጡ መንግሥት አይቶ እንዳላየ አለፎዋቸዋል።

ከጅምሩ ሕዝብን ሲይሰቃዩ የኖሩት የወያኔ ዘራፊ አውሬዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ለፍርድ መቅረብ ሲገባቸው የዘረፉትን ይዘው እንዲቀመጡ መደረግ አልነበረባቸውም። የሜንጫ ጭፍጨፋን ሲሰብኩ የነበሩ አክራሪዎችና ሌላውን ብሔረሰብ በተለይ አማራውን “ነፍጠኛ” በሚል ዘር ከዘር፣ ሃይማኖት ከሃይማኖት የሚያጋጩ መርዘኞች በሩ ወልል ብሎ ተከፍቶላቸው በማናለብኝነት እንዲፈነጩ የተፈቀደላቸው በዚህ መንግሥት ነው። እነዚሁ ተረኛ ፅንፈኞች ከመዲናዋ በቅርብ ርቀት ሳይቀር ሕዝቡን ሲያፈናቅሉና እጅግ ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ በማንነታቸውና በዕምነታቸው እየተመረጡ ሲፈጁ፣ የፀጥታ አስከባሪው ከእነርሱ ብሔር የወጣ በመሆኑ ሲተባበራቸው፣ በአንፃሩ ግ “አድኑኝ” የሚለውን ወይም ራሱን ለመከላከል የሚሞክረውን ከእነርሱ ዘር ያልሆነውን ሕዝብ እየደበደቡ ዘብጥያ ሲያወርዱ ታይተዋል። በችሎታ ሳይሆን በብሔራቸው የተጎለቱ የኦሕዲድ ካድሬዎች ከንቲባዎች ካልጠፉ መሬት ሌላ አማራጭ ሳይሰጡ ንፁሐን ለፍቶ አደሮች ከነሕፃናቶቻቸው በላያቸው ላይ በክረምቱ ወራት ቤታቸውን በማፍረስ በገዛ ሀገራቸው እንደውጭ ጠላት ከተጠለሉበት ቤተክርስቲያን ሳይቀር የኦሮሚያ ፖሊሶች እየተከተሉ በዱላ ሲቀጠቅጧቸው የአብይ መንግሥት አይቶ እንዳላየ፣ ሰምቶ እንዳልሰማ ጆሮ ዳባ ልበስ ላል።

 “On dort tranquille parce que les cris des autres n’arrivent pas jusqu’à nos oreilles”

Le Ventre de l’Atlantique

(The Belly of the Atlantic) ከተባለው የሴኔጋል ፈረንሳዊት ጸሐፊ ፋቱ ም መጽሐፍ የተወሰደ።

ትርጉም“የሌሎች ጩኸት እስካልረበሸን ድረስ በሰላም እንተኛለን።”

የእኛውም የአራት ኪሎ መንግሥት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰቆቃ ውስጥ ሆኖ ሕግ ይከበር እያለ ሲጮህ ሰምቶ እንዳልሰማ ተኝቶ ከርሞ እንዳልነበር አሁን ተጠናክረው በመምጣት መንበረ ስልጣኑን ለመቀማት የአራት ኪሎን በር ሲያንኳኩ ያዙኝ ልቀቁኝ ማለት ጀምሯል።

“Fools multiply when wise men are silent.”

Nelson Mandela.

የአዲስ አበባ ከንቲባ ሕግን ተከትሎ በሕዝብ ይሁንታ የተሾመ አለመሆኑ ይታወቃል። ከንቲባው በተከናወኑ የልማት ሥራዎችአካባቢ በቴሌቪዥን መስኮት የሚያሳልፍባቸው ጊዜዎች በርካታ ናቸው። የተጎዱ ሲረዳ፣ የተራቡ ሲያጎርስ የሚታይ ቢሆንም በጓሮ በር የራሱን ብሔር በአድሎዋዊነት እየጠቀመ፣ የራሱን አጀንዳ በመተግበር፣ ርካሽ ተወዳጅነትን ለማትረፍ ሲሯሯጥ ይታያል። አማርኛ የሀገሪቱ በሔራዊ ቋንቋ እንደመሆኑ መጠን ማዛጋጃ ቤቱም ተገልጋዮችን በዚሁ ማስተናገዱ እየታወቀ ከኦሮሚያ ክልል አማርኛ የማይናገሩ የኦሮሞ ተወላጆችን አምጥቶ በመቅጠር መሥሪያ ቤቱን ያተራምሳል፤ ተገልጋዮችን ያጉላላል።

የአዲስ አበባ ነዋሪ ከራሱና ከልጆቹ አፍ ቀንሶ፣ አንጀቱን አሥሮ የሠራውን የኮንዶሚኒየምና የ40/60 መኖሪያ ቤቶች የከተማዋ ነዋሪ ላልሆኑና አንድ ሳንቲም እንኳን ላላዋጡ የኦሮሞ ተወላጆች ከአጋር መሥሪያ ቤቶች ዕውቅና ውጪ በሥልጣኑ እንዲሰጥ አድርጓል። ሌላውን ነገድ አባላት እያባረረ፣ የኦሮሞ ወጣቶችን ግን ተደራጁ እያለ የከተማዋን መሬት እየሸነሸነ የመሬት ወረራ ያካሂዳል። የአዲስ አበባን ሕዝብ ስብጥር ይዘት በኦሮሞ የበላይነት ለመቀየር ሲል ከኦሮሚያ ገጠር ከተሞች ሳይቀር ወጣቶችን ወደ አዲስ አበባ በማስመጣት የአዲስ አበባ ነዋሪነት መታወቂያ ወረቀት በሕገወጥነት እንዲታደላቸውና የአዲስ አበባ ነዋሪ እንዲሆኑ አድርጓል። ኢትዮጵያ የብዙ ነገዶችሀገር እንደመሆኗ መጠን ሁሉንም ያቀፈ፣ የሥራ ዕድልም ሆነ ተጠቃሚነት ማስፈን ሲገባ ዓይን ያወጣ አድልዖ የሚፈፀመው በለማ መገርሣ በግልፅ እንደተነገረው የአዲስ አበባን ዴሞግራፊ የመቀየሩ ሥራ በስፋት እየተካሄደ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ እኩይ ተግባር ነው።

እነዚህ ሕገወጥ ሠፋሪዎች እነ ጃዋር ውሃ ቀጠነ ባሉ ቁጥር ጃስ እያሉ የከተማይቱን ነዋሪዎች እንዲያዋክቡ፣እንዲያሸማቅቁ፣ እንዲዘርፉና እንዲገድሉ ያደራጇቸው እጅግ ዘረኛ ፁም ሰብዓዊነት የሌላቸው ቦዘኔዎች ናቸው። በሌላ በኩል ሕዝቡ ከእነዚህ አውሬ መሰል ሰዎች እራሱን ለመከላከል ሲሞክር የፀጥታ አስከባሪዎች እንደወንጀለኛ እየገፈተ፣ በዱላ እየቀጠቀጡ እሥር ቤት ያስገቡታል። በመስቀል በዓል ወቅት ቄሶች ከበሯችሁ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ አሥራችኋል በሚልና የውጭ ቱሪስቶችን የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ይዛችኋል ተብለው ሲዋከቡና ሲገፈተሩ ውለዋል። በኢትዮጵያ ታሪክ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ መያዝ እንደወንጀል የተቆጠረበት ዘመን ቢኖር አሁን ነው።

ሚዛናዊነትን ባልጠበቀ መልኩ በአንድ ብሔር ላይ ብቻ ያተኮረ የፖሊስ ሠራዊት ምልመላ ይካሄዳል። በሕግ አስከባሪነት መቀጠር የሌለባቸው የኦነግ አባላት በሠራዊቱ ውስጥ እንዲሰገሰጉ ተደርገዋል። ከልጅነታቸው ጀምሮ በሌላው ብሔር ላይ ጥላቻን ሲጋቱ (Brain washed የተደረጉ) ያደጉ ሚዛናዊ ሆነው ሕግ ያስከብራሉ ብሎ ማሰብ “ድመት መንኩሳ፣ ዓመሏን አትረሳ” የተባለውን መርሣት ነው የሚሆነው። በተለያዩ ጊዜያት ገጀራና ዱላ ይዘው ከተማ ሲበጠብጡ የነበሩ ፅንፈኞች በአዲስ አበባ ፖሊስነት ተመልምለው በኢንጂነር ታከለ ዑማ ከተመረቁ በኋላ ሥራ ይዘው አይተናል

ከአሸባሪነት ልብስ ብቻ ቀይሮ ወደ ፓሊስነት

 የብዙ ዓመታት ዕድሜ ጠገብ የሆኑት የታሪክ ባለቤት የሆኑ ህንፃዎች በልማት ስም ካለአጋር መሥሪያ ቤቶች ዕውቅና ውጭእንዲፈርሱ ትዕዛዝ የሚሰጠው በአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ነው። በጣሊያን ወረራ ወቅት ለላቦራቶሪ መርምር የተገነባው አንበሣ መድሃኒት ቤት፣ ከጎኑ የገኘው ኔኦን አዲስ የፍርድ ቤት ውሳኔ ተጥሶ፣ ዋቢ ሼበሌ ጎን ሎምባርዲያ ምግብ ቤት የሚገኝበት ማይጨው አደባባይ ያለው ሕንፃ ፈርሶ የኦሮሚያ ባንክ እንዲሠራበት ትዕዛዝ ወጥቶበታል። በአጭሩ በልማት ስም ቅርስ የማጥፋት ዘመቻ እየተካሄደ ነው።

የጃዋር ቄሮ የኢትዮጵያ ታሊባን፣ አይሲስ፣ አልሽባብ ወይስ ቦኮሐራም?

“አንበሣ ተኝቶ ጊደር ሸናችበት

ከምን ያለው ጊዜ እኛ ደረስንበት።

ያንበሣ ልጅ ሞቶ የጅብ ልጅ ገነነ፣

አላሳልፍ አለ ፀጉሩ እየበነነ።”

(ወይ ሀገሬ ከሚለው የሊቀ ማዕምራን አበባው ይግዛው ግጥም የተወሰደ።)

የወያኔን ፋሺስታዊ ዘራፊ ቡድን ለመታገል ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ በአንድ ላይ ሆ! ብሎ በመነሳት ከፍተኛ መስዋዕትነት ከፍሏል። ወጣቱ ፋኖ፣ ዘርማና ቄሮ የተለያዩ የትግል ስሞችን በመጠቀም በየአካባቢው ተደራጅቶ ለዕሥር፣ ስቃይና መስዋዕትነት እራሱን ሳይሰስት ሰጥቶ ሙሉ ለሙሉ ባይወገዱም አውሬዎቹን ሕዎሓቶች ዘወር ለማድረግ በቅቷል።

በድሉ ማግሥትም በታሪክ አጋጣሚ በትረ ስልጣኑን የያዘው መንግሥት ዴሞክራሲን አሰፍናለሁ በሚል ከሀገር ውስጥ የፖለቲካ እሥረኞችን ነፃ ሲለቅ፣ ከውጭ የነበሩ ተቃዋሚዎችን ግማሹን ትጥቅ አስፈትቶ፣ የተቀረውን ደግሞ ለራስ ወገን በማዳላት ከነትጥቁ ሀገር ውስጥ አስገብቷል። እንደ ጃዋር ያሉት ጠባብ ፅንፈኛ ዘረኞችም የመርዝ ምላስ ጠብመንጃቸውን ዘው ወደ ሀገር ውስጥ ከመግባታቸውም በላይ የመገናኛ ብዙሐን ፈቃድ ተሰጥቶዋቸው ለእነሱ አጥፊ ፖለቲካ የሚጠቅማቸውን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ናዳ በኢትዮጵያ ታሪክ ሲያወርዱ ከርመዋል።

እነጃዋር ቀደሞ ሲል ለኦሮሚያና ለኦሮሞ ሕዝብ ሲታገል ቆየው ቄሮ የተባለውን ቡድንም ከጎናቸው በማሰለፍ ለእኩይ ተግባራቸው ሲያዘጋጁትና ሲያደራጁት ከርመዋል። በመሆኑም በተለያዩ ጊዜያት እነርሱ በሚሰጡት መመሪያ መሠረት ኦሮሚያ ውስጥ የሌላ ብሔረሰብ አባላትን ሲያጠቃ ቆይቷል። ለመሆኑ የገቢዎች ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት የዛሬዋ አቃቤ ሕግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ለኦ ኤም ኤን (O.M.N.) በተለዬ ሁኔታ ስላበረከቱት 58 ሚሊዮን ብር ማን ይሆን የሚጠይቃቸው? እርሳቸው ይህንን ያክል ከፍተኛ ገንዘብ ከታክስ ከፋዩ ሕዝብ ላይ ወስደው የሰጡት የሚዲያ ማዕከል ከሚዲያ ሕግ ውጭ ሄዶ የዘር ፍጅት በመቀስቅሱና በዚያም ምክንያት ፁሐን ሰዎች በፅንፈኛ የቄሮ አባት ከፍተኛ ጭፍጨፋ ስለተፈፀመባቸው ሀገር ቤት ያለው ኦ ኤም ኤን ሲታገድ ጋዜጠኞችም ሆኑ ባለቤቱ አቶ ጃዋር ዘብጥያ ወርደዋል። ለማንም ሚዲያ ያልተደረገ ዕርዳታ ከሀገሪቱ ሕግ ውጭ ከመንግሥት ካዝና አውጥተው ለኦ ኤም ኤን የሰጡት ወይዘሮ አዳናች አቤቤስ መቸ ነው የሚጠየቁት? ይህ ተግባራዊ ካልሆነ ደግሞ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በአቃቤ ሕግ ሃላፊነታቸው በO.M.N. ላይና በጋዜጠኞች እንዲሁም በባለቤቱ ላይ ለሚመሠረተው ክስ ምን ያህል ገለልተኛ ናቸው ብሎ የኢትዮጵያ ሕዝብ ማመን ይችላል?

የጃዋር ቡድጣቱ ብቻ ሳይወሰን በመንግሥት ባለስልጣናትና በፀጥታ ኃይሉ ውስጥ ሰርጎ ገብቶ ደጋፊዎች በመመልመል የማንአለብኝነት ድርጊት ከመፈፀም ባሻገር በገሀድ ዓይኑን በጨው አጥቦና በማን አለብኝነት አብጦ ይህን ታላቅ ሕዝብ ከአብይና ከለማ ቀጥሎ የእኔ (የቄሮ) መንግሥትነው የሚያስተዳድረው ል ሃይ ባይ የጠፋበት ምክንያቱስ ምን ይሆን? ያኔ ለጃዋር በአንድ ሀገር ውስጥ አንድ መንግሥት ብቻ ነው ያለውና ልክህን ዕወቅ ቢባልና መንግስታዊ የእርምት እርምጃ ተወስዶ ቢሆን ኖሮ አሁን የደረስንበት ችግር ላንደርስ እንችል ነበር። ነገር ግን ኦሮሞን ኦሮሞ እንዲያጠቃው አልፈልግም የሚል የፀና ዕምነት ያላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ይህንን የመሰለውን እብጠትና ሕገወጥነት እንዳልሰማ በማለፍ ማሳደድና ግልፅ ጦርነት ውስጥ መግባት የፈለጉት ከሰላምና ዴሞክራሲ ጠበቃው እሥክንድር ነጋ ጋር ነበር።

“ኧረ ቆሉብን፣ ኧረ ፈጩብን፣

እንጠብቃለን እስኪያቦኩብን።”

ይ ሀገሬ ሚለው ግጥምየተወሰደ

Pashto ወይም Pukhto በምሥራቅ ኢራን የሚነገር ቋንቋ ነው። በአፍጋኒስታን ሽቱን የሚባለው ግዛት ነዋሪዎች የፓሽቶ ቋንቋ ተናጋሪ ሲሆኑ እ.አ.አ. በ1994 የአፍጋኒስታን መንግሥት ተቃዋሚ ከነበረው ሙጃህዲን ከሚባለውና በጎበዝ አለቃ ከሚመራው ተቃዋሚ በመገንጠል በአብዛኛው ወጣቶችን ያቀፈ ታሊባን የሚባለው አማፂ ቡድን ተፈጥሮዋል። በፓሽቶ ታሊብ ማለት ተማሪ ማለት ሲሆን፣ ታሊባን የሚለውም ስያሜ የመጣው ከዚሁ ነው።

ታሊባን በፓኪስታን፣ ሳዑዲ አረቢያና በተባበሩት አረብ ኤምሬት የሚረዳ ሲሆን፣ አፍጋኒስታንን በኋላ ቀር የሻርያ የእስልምና ሕግ ጨቁኖ ለመግዛት የሚታገል ፅንፈኛ ቡድን ነው። ታሊባን የመንጋ ፖለቲካ የሚከተል የጭፍኖች ስብስብ ሲሆን፣ የእርሱን አመለካከት የማይቀበሉትን ሁሉ በፈንጂና በጥይት የሚቆላ ጨካኝ አክራሪ ቡድን ነው። በአርዕሥቱ ላይ የጠቀስኳቸው የተቀሩት ፅንፈኛ ቡድኖችም በሕግ የበላይነት፣ በዴሞክራሲና በሰው ልጅ ነፃነትና እኩልነት የማያምኑ ኋላቀር ጨካኝ ቡድኖች ናቸው። እንግዲህ ሀገር ውስጥ የገባው የጃዋር ጀሌም አመሠራረቱ ይህን ተሞክሮ በመውሰድ ነው የሌላ ብሔር ተወላጆችንና የሸዋ ኦሮሞ ክርስቲያኖችን ሲጨፈጭፍ፣ ቤታቸውን ሲያቃጥልና ንብረታቸውን ሲያወድም የሰነበተው።

Acephalous Society (ቃሉ የግሪክ ነው) የፖለቲካ መሪ ወይም መዋቅር ሳይኖረው በመንጋ ወይም በብሔር በመደራጀት ውሳኔዎችን በስምምነት የሚያስተላልፉ ናቸው። “መንግሥት አልባ” ማህበረሰብ ልንላቸው እንችላለን። ሥርዓት አልበኝነትን (Anarchy) በሕግና በሥርዓት የማይመራ የመንግሥት አካል የማይቆጣጠረው ሕብረተሰብ የሚፈጥረው ቀውስ ነው። አናርኪዝም ጃዋራውያን በሚያደርጉት ቅስቀሳ እየተነዱ የሕግ የበላይነትን ገፍትሮ በመጣል በሀገሪቱ ላይ ችግር ለሚፈጥሩት ሥርዓት አልበኞች የሚመጥን ቃል ነው። ብዙ የሚወራለት ኋላ ቀር 21ኛው ክፍለ ዘመን የማይመጥነውና ሆኖም ግን “ስለጥሩነቱ” ሲጮህለየሚዋለው የገዳ ሥርዓትም ከዚሁ ጋር ተመሳሳይነት አለው። የገዳ ሥርዓት በዩኔስኮ ተመዝግቦ ለትውልድ የምናወርሰው ድንቅ ሥርዓት ሳይሆን በፍፁም ጭካኔውና የሰውን ልጅ መብት ገፋፊነቱ ሊወገዝ የሚገባው ሥርዓት ነው። ይህንን የሚያሣይ ጥቂት ምሣሌዎችን ልጥቀስ፦

1. የገዳ አመራር አባላቱ በየ8 ዓመቱ ስልጣኑን ለሚቀጥለው ተረካቢ ሲያስረክብ እርሱ ከሰምንት ዓመት በፊት ከተረከበው የግዛት ክልል ተጨማሪ ወረዳዎችን ወይም አውራጃዎችን ርሮ የኦሮሞ የግዛት አካል በማድረግ ማስረከብ አለበት። ይህ የገዳ ሕግ ተግባራዊ ይሆን ዘንድ አጎራባች አውራጃዎችና ክፍላተ – ሀገራት የግድ መወረር አለባቸው።
2. በወረራ የተያዘው ሀገር ላይ የሚኖሩ ነገዶች በሞጋሣ ሕግ መሠረት ነገዳቸውን ተገደው እንዲቀይሩ ይሆኑና ኦሮሞ ይሆናሉ። ተገዶ ማንነትን መቀየር ምን ያህል ኢሰባዊ ድርጊት እንደሆነ ማንም ሊገምተው ይችላል።
3. አንድ ሰው የገዳ አመራር አባል ለመሆን ከሚያስችሉት መሥፈርቶች ውስጥ፦ ዕድሜው 48 ዓመት እንዲሆንና ከኦሮሞ ውጭ የሆነን ሰው ገድሎ ስልብ አለበት ወይም እንደ አንበሣ፣ ነብር፣ ዝሆንና ቀጨኔ የመሳሰሉትን የዱር እንስሳት መግደል አለበት።
4. በገዳ ሥርዓት ጊዜ ኦሮሞዎች የሚገረዙት በ48 ዓመታቸው ነው። ከግርዛት በፊት የሚወለዱ ህፃናት ጫካ መጣል አለባቸው። የተጣሉትን ህፃናት አንስቶ የሚያሳድግ ሰው ቢገኝ ይወገዛል፤ ይቀጣል።
5. የገዳ ሥርዓት የወንዶች ብቻ ሲሆን ሴቶችን አያሳትፍም ነበር።
6. አንድ ሰው ፀጉሩን ለመላጨት፣ ቅቤ ለመቀባት፣ ወይም ሚስት ለማግባት ከኦሮሞ ውጭ የሆነ ሰው መስለብ አለበት።

የዛሬዎቹ የኦሮሞ ፅንፈኞች ገዳን ሲያሞካሹና በገዳ ሥርዓት መመራት አለብን ሲሉ ይህን የመሰለውን እጅግ ጨካኝ፣ ኢሰባአዊና ኋላቀር ሥርዓትን በ21ኛው ክፍለዘን ላይ አምጥተው ሊጭኑብን ስለፈለጉ ነው። የሚያሳዝነውና የሚገርመው ግን ዩኔስኮ ይህንን የመሰለውን ጨካኝና ዘግናኝ ሥርዓት በዓለም ቅርስነት መመዝገቡ ነው።

ኢትዮጵያ በቀንድ ከብት ብዛት በዓለም ከፍተኛውን ደረጃ የያዘች ሀገር ናት። ይህ ቁጥር ባለአራት እግር እንስሳትን ብቻ ሳይሆን እንደክብት መንጋ ዱላ እየያዙ የሚሮጡትንም ባለሁለት እግር እንሦች ይጨምራል። የከብት መንጋ ከኋላ እየተነዳ ሲሮጥ በመንገዱ ላይ ፋት እያደረሰ እንደሚያልፍ ሁሉ ከቀየው ሲወጣ ለምን ዓላማ፣ ለማን መጠቀሚያነት ሳያውቅ ባለሁለት እግሩ ከብት ግር እያለ ሌላውን ተከትሎ ዱላ ይዞ ጥፋት እያደሰ ሲሮጥ ነው የሚውለው። ይህ መንጋ ዓላማ ቢስ ስለሆነ እንደግሪሣ ወጥቶ አንድ ጥይት ሲተኮስ እንደ ረሽ ጥይት በየአቅጣጫው የሚባታተን ነው።

“የእህል ጥሬ በእሣት ያበስሉታል፤ የሰው ጥሬ ምን ያደርጉታል?” በውጭና በሀገር ውስጥ የሚኖሩ ፕሮፌሠር ተብዬ የኦሮሞ አክራሪ ፅንፈኞችም ቢሆኑ ውሃ የማይቋጥር ጉንጭ አልፋ መርዘኛ ፕሮፓጋንዳ ከመንዛት ያለፈ የበሰ የሀሳብ ፍጭት አያደርጉም። ትናንት፣ ዛሬ፣ ነገም የሚያላዝኑት ከተለመደ ነፍጠኛና ሚኒልክ ላይ   የማይወርድ የሙሾ ድርደራ ነው። አብዛኛዎቹ በሉተራን ሚሲዮኖች ቤት ከልጅነታቸው ጀምሮ እየተላላኩ በቤት ሠራተኛነት እናት ጡት ሳይሆን በዱቄት ወተት ስላደጉ የሀገራቸውን ታሪክ ያስተማረ ወላጅ ስላልነበራቸው ኢትዮጵያ ማለት እናት ማለት እንደሆነች አይገባቸውም። ሚሲዮናውያኑ የቄስ ካባ ለብሰው ሰላዮች ስለነበሩ ለእኩይ ተግባራቸው ይመጥናሉ ብለው የመረጧቸውን ሀገራቸው በማደጎነት ወስደው የራሣቸውን ሃይማኖት ተከታይ በማድረግ ቀርፀዋቸዋል። ሰው ያልዘራውን አያጭድም እንደሚባለውም “Down, Down Ethiopia!” እያሉ ሰሞኑን የሚጮሁትም የእነኚሁ ቡችሎች ናቸው።

በኢትዮጵያ ላይ ብቻ ሳይሆን በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ላይም ከፍተኛ ጥላቻ አላቸው። ለኢትዮጵያ ሀገራቸው በጀግንነት የወደቁ የኦሮሞ አርበኞችና ታዋቂ ሀገር ወዳድ የኦሮሞ ተወላጆችን “ነፍጠኛ” በማለት ሲያወግዙ እንጅ እንደ ዜጋ ሲያወድሱ አይሰሙም። በቅርቡ የተሰዋው አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሣም በእነርሱ የወጥመድ ቀለብት ውስጥ ገብቶ በግፍ የተሰዋውም ኢትዮጵያዊነትን ከፍ አድርጎ ስለሚኮራበት ነው። ነፍጥ ማለት ጠመንጃ ማለት ሲሆን፣ ነፍጠኛ ማለት ደግሞ መሣሪያ የታጠቀ የሀገር ዳር ድንበር ጠባቂ ማለት ነው። ነፍጠኛ በማደጎ ልጆች የሚጠላው ሀገር ወዳድ፣ ድንበር አስከባሪ ስለሆነ ነው። ነፍጠኛ ሀገሩን የሚወድ (Patriot)የሀገሩን ጥቅም አሳልፎ የማይሰጥና የማይደራደር ስለሆነ በፈረንጆቹ ዘንድም አይወደድም። Patriot ወይም ሀገር ወዳድ ሕዝብ በፈረንጆቹ ዘንድ የማይወደደው ለዘረፋቸው በር ስለማይከፍት ስለሆነ እንደዚህ ያለ መሪ ሲፈጠር ቶሎ ያጠፉታል። የቀድሞዋ Upper Volta የአሁኗ Burkina Faso መሪ የነበሩት ቶማስ ሳንካራ፣ የኮንጎው ፓትሪስ ሉሙምባ ከላቲን አሜሪካ የቺሊው ሳልቫዶር አየንዴ በሴራና በግፍ የተሰውት ሀገር ወዳድ በመሆናቸው ው።

ትፋቱ የሚመለሰው የሰው ልጅ ሳይሆን ውሻ ብቻ ነው። በአውሮፓ፣ በአሜሪካና አውስትራሊያ የራሳቸውን ጥሩ ኑሮ እየኖሩ ከዘረፈውና የኢትዮጵያን ሕዝብ፣ በተልይ ኦሮሞውን ሲያሰቃይ ከኖረው ከወያኔ ቡድን ጋር

አብረው ኢትዮጵያ ላይ የጥፋት ጥሩምባ ሲነፉ የሚውሉት ሀቀኛ የፖለቲካ ሰዎች ሳይሆኑ በታሪካዊ ጠላታችን በግብፅ የተገዙ ባንዳዎች ናቸው።  አብረው ኢትዮጵያ ላይ የጥፋት ጥሩምባ ሲነፉ የሚውሉት ሀቀኛ የፖለቲካ ሰዎች ሳይሆኑ በታሪካዊ ጠላታችን በግብፅ የተገዙ ባንዳዎች ናቸው።

የተፉትን የላሱት ባንዳዎች ጥምረት

በ21ኛው ክፍለ ዘመን ዜጎችን የሚጨፈጭፈው መላውን ቤተሰብ በተኛበት በእሣት የሚያጋየው፣ ዓይን ጭካኔ ጎልጉሎ የሚያወጣው፣ አስከሬን በገመድ የሚጎትተው፣ ሰውነትን ቆራርጦ የሚገድለው፣ ዛፍ ላይ ሰውን ዘቅዝቆ የሚሰቅለው፣ የሚዘርፈውና ንብረት የሚያቃጥለው፣ ፋብሪካና የመንግሥት መሥሪያ ቤት እያቃጠለ የራሱን ብሔረሰብ አባላት ሥራ ፈት የሚያደርገው፣ የጤና ተቋማትን፣ ትምህርት ቤቶችን የሚያነደው ዘረኛ የእስልምና ሃይማኖት አክራሪ የኦሮሞ ፅንፈኛ ነው። በሰለጠነው ዓለም ውስጥ እየኖሩ እንዳደጉበት ኋላ ቀር የባሌ፣ አርሲ፣ ጂማ፣ ቦረና ወ.ዘ.ተ. የገጠር ከተሞች ያስቡ ያልበሰሉ የእስልምና ሃይማኖት አክራሪ ኦሮሞዎች በወያኔዎች ተባባሪነት ከአልሽባብ ሶማሌዎች ጋር የኦነግን ሰንደቅ ዓላማይዞ በመውጣት ያስጠጋቸውን ሀገር ሕዝብ ሲበጠብጡ መታየት ጀምረዋል። ለንደን የኢትዮጵያን ኤምባሲ ከበው የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ አውርደው የኦንግን ጨርቅ ለመስቀል ሞክረዋል። ለአገልግሎት የመጣ ኢትዮጵያዊደብድበዋል። እንግሊዞች የሠሩትን የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴን ሀውልት ሰብረው የፓርኩን ንብረት አውድመዋል። እነዚህ ጥሬዎች የረሱት በኤምባሲው በራፍ ላይ የቆመው ፖሊስ ደረቱ ላይ በተሰካው ካሜራ ሲቀርፃቸው እንደነበርና አካባቢው የብዙ ሀገር ኤምባሲዎች መገኛ ስለሆነ በCCTV ካሜራ የታጠረ መሆኑን ነው። በቅርቡ ውጤቱን እንሰማለን። ከብቶቹ በሚኒሶታ አውራ መንገድ ዘግተው ችግር በመፍጠራቸውም ዋጋ አስከፍሏቸዋል።

እነኝህ ማፈሪያዎች ሚኒሶታ ኢትዮጵያውያንን ሲደበድቡና በሲያትል ደግሞ አንድ ነጭ አሜሪካዊ ወጣት በቡድን ሜዳ ላይ ጥለው ሲቀጠቅጡ፣ የኦነግን ሰንደቅ ዓላማ የያዙ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ኦሮሞና ሶማሌ ሴቶች ከእነ ሂጃባቸው፣ ወንዶቹ ከእነ ጀለቢያቸው በቪዲዮ ተቀርፀው ታይተዋል። አንዲት ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊት የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ይዛ በመገኘቷ በመኪና ገጭተው ለማምለጥ ሲሞክሩ በፖሊስ ተይዘዋል። ካናዳ ካልጋሪ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ በሚያደርጉበት ጊዜ አንድ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ቀለም ያለው ቲሸርት የበሰ ኢትዮጵያዊ ወጣት ሰልፉን ቪዲዮ መቅዳት ይጀምራል። በካናዳ ይሄ የተከለከለ አይደለም። ፖሊስም አጠገቡ አለ። ግሪሣዎቹ ይህንን ወጣት እያባረሩ መደብደብ ይጀምራሉ። ፖሊሱ ሊያድን ሲሞክር እንስሳዎቹ ፖሊሱን አብረው ሳይጎሽሙት አልቀሩም። ሌሎች ፖሊሶች በሳይክል ተሯሩጠው መጥተው በማዳን አጥፊዎቹን አሥረው ይወስዳሉ። የሀገሪቱን አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጥሰው ሰልፍ በመውጣት “ኢትዮጵያ ትውደም (Down Down Ethiopia) ሲሉ የዋሉ በዱባይ ኢትዮጵያውያን የቤት ሠራተኞች ላይ የተወሰደው እርምጃ ደግሞ የኢትዮጵያ አምላክ ፈጥኖ መፍረዱን እያሳየን ነው። እነዚህ የናት ጡት ነካሽ የቤት ሠራተኞች እስከአሁን ታሥረው ከቆዩ በኋላ እያንዳንዳቸው 3 ሺህ ድራም ቅጣት ከፍለው ትውደም ወዳሏት ኢትዮጵያ ሊባረሩ ነው። የጊዜ ጉዳይ እንጅ ሁሉን የሚያየው እግዚአብሔር በሁሉም የኢትዮጵያ ጠላቶች ላይ ይርዳል።  

ነብሱን በአፀደ ገነት ያኑረው፣ ለቤተሰቦቹ፣ ዘመዶቹና ወዳጆቹ መፅናናትን ይስጥልንና የአርቲስት ሀጫሉን ህልፈት ተከትሎ ስለተፈፀሙት እኩይ ተግባራት ሁላችንም የምናውቀው ስለሆነ መደጋገሙ አስፈላጊ አይሆንም። ሆኖም ከምንም በላይ የሚያሳዝነው ደግሞ ለአንድ ሀጫሉ ያ ሁሉ መታሰቢያ ሲደረደርለትና ለቤተሰቡ መቋቋሚያ በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች አማካኝነት የገንዘብ መዋጮ እንዲደረግለት ሰርኩላር ደብዳቤ ሲላክ፣ በማነነታቸውና በዕምነታቸው በፅንፈኛ ቄሮዎች ለታረዱት እስከ 800 ለሚደርሱ ወገኖች ግን ምንም ዓይነት እውቅና መስጠት አልተፈለገም። የመንግሥት ሚዲያዎችም ስለጠፋው ንብረት ሲዘረዝሩ በግፍና በጭካኔ ስለታረዱት ወገኖች ግን መዘብ አልፈለጉም። ይህም ከመንግሥት የወረደ መመሪያ መኖሩን አመልካች ነው። የሚያስተዳድረውን ሕዝብ በዕኩል ዓይን የማያይ መንግሥት ደግሞ የአፓርታይድን ሥርዓት የሚያራምድ ዘረኛ መንግሥት ነው።  

 በሕግ በተያዘ ጉዳይ ላይ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ተጠርጣሪዎችን በተመለከተ አስተያየት መስጠቱ ተገቢ ላይሆን ይችላል። ሆኖምግን የፀጥታና የሕግ አስከባሪ ባለስልጣናትን መገለጫዎች በተመለከተ የተምታቱና አስቀድሞ የመፈረጅ ምልክቶች ይታያሉ። ብዙ ደጋፊ አላቸው ተብሎ የሚወራላቸው ግለሰቦች ስለተያዙ ሌሎቹን እንደማካካ ወይንም ቁጣ ማብረጃ መናጆ የማድረግ ሁኔታ ይታያል። የእሥር አያያዝንም በተመለከተ በአድሎአዊነት የሚደበደቡ፣ የሚገፈታተሩና ሰብዓዊ መብታቸው የሚጣስም በፍርድ ቤት አቤት ሲሉ ይሰማልና ሊታሰብበት ይገባል። ቀደም ሲል ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆኑ ከንቲባው ጥርሳቸውን የነከሱባቸው ግለሰቦች ላይ ይህ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተፈፀመ መሆኑ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው አድርጎታል።

 በሕገ መንግሥቱ መሠረት ሰላማዊ ሰልፍ ለመጥራት በጊዜ ማሳወቅን ብቻ ነው የሚጠይቀው። በዚሁ መሠረት ባልደራስ ሰላማዊ ሰልፍ ስለጠራ ገና ለገና ከአማራ ክልል ሰልፈኞች ይመጣሉ ተብሎ ታስቦ በአናርኪስቱ የቄሮ መንጋና በኦሮሚያ ፖሊስ ድጋፍ ከአማራ ክልል ወደ መሀል ሀገር የሚገቡ መንገዶች ኦሮሚያ ላይ በድንጋይ እንዲዘጉ ተደርጓል። የባልደራስ ጽ/ቤትም በፖሊስ ተከቦ በተለያዩ ጊዜያት ከከንቲባው ጎን የተነሱት ፎቶ ያላቸው (በተለይ ቀንደኛ የሆነው ጊዜ ያለፈበትን አፍሮ የሚጠቀመው ኦብሳ) የቄሮ መንጋዎች ጥሰው በመግባት ረብሻ ፈጥረዋል። በወቅቱም ወደተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የሚገቡ ወጣቶች መንገድ ተዘግቶባቸው ሜዳ ላይ እንዲያድሩ ተደርጓል። “የላጪን ልጅ ቅማል በላት” እንዲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እራሳቸው የሚጠቀሙበትን ቃል ልዋስና የጀዝባዎች የፖለቲካ ሸፍጥ ተካሂዷል። እንደዚህ ዓይነት Petit (ተራ)ማጭበርበር የሚሠራ መንግሥት በዕኩልነት ወደ ዴሞክራሲ ያሻግረናል ብሎ ለማሰብ ይከብዳል።

በአንድ በኩል በቴሌቪዥን መስኮት እንደቦክሰኛ ደረታቸውን ነፍተው የV8 በር ሲከፈትላቸውና በሌላ በኩል ደግሞ በካቴና ተቆራኝተው አንገታቸውን የደፉ ተጠርጣሪዎች መታየቱም በሕግ ፊት ሁሉም እኩል ነው የሚለውን የሚያሳይ አይደለም። የፀጥታ ባለስልጣናትም በሚሰጡት መግጫ ምንም የሕግ ጥሰት ተጠያቂነት የሌለው የመገናኛ ብዙሐንና በሕግ ተመዝግቦ በመንቀሳቀስ ላይ ያለን የፖለቲካ ፓርቲን ስም በስህተት መጥቀሳቸው እነኚህ የሥራ ሀላፊዎች በእውነት በሚዛናዊነት ሃላፊነታቸውን ይወጣሉ ወይ? የሚል ጥያቄ በብዙዎች ዘንድ ሳያጭር አላለፈም።

 አቶ ጃዋርም ለፍርድ ቤቱ አርቆ የማየት ችግር አለብኝ፤ ዘመዶቼን እንኳን በሩቁ ለመለየት አልቻልኩም በማለት አቤቱታ አቅርበዋል። ይሄ የጤና ችግራቸው ዕውን ከሆነ አሁን ከእርሳቸው አንደበት ወጣ እንጅ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርቀው እንደማያዩ አስቀድሞ የሚያውቀው ስለሆነ እንደፍርድ ማቃለያ ቢመዘገብላቸው በወህኒ ዘመናቸው በሩቁና በሰፊው የማየት ችሎታ አካብተው እንዲመጡ አስፈላጊው ትዕዛዝፍርድ ቤቱ ቢሰጥላቸው መልካም ንው

የሕዳሴውን ግድብ ሙሌት አስመልክቶ ግብፅ ኢትዮጵያን ለማስፈራራት የተለያዩ የጦር ትርኢቶችን በማሳየትና በጯሂ የአረብ ጋዜጠኞች ስትንጫጫብን ከርማለች። በአንፃሩ የኢትዮጵያ መንግሥትና የጦር ኃይል አይበገሬ መሆኑን ድምፁን ከፍ አድርጎ ሞራላችን እስከ አንገታችን እስከሚደርስ ድረስ ሲያቅራራ ሰንብቷል። ታዲያ ጥቂት ውርጋጦች በተወሰኑ የሀገሪቱ ክፍሎች ይህን ሁሉ እልቂትና ውድመት ሲፈፅሙ ያ ሁሉ ፉከራ የት ደረሰ? (ከሻሸመኔ 20 ኪሎሜትር በማይሞላ እርቀት ላይ ከፍተኛ ጦር እንደነበረ ተሰምቷል)። የደህንነትና የፖሊስ ሠራዊቱስ በኮቪድ 19 ሥርጭት ምክንያት ሥራ አቁመው ነበር ማለት ነው? እኛ የፈራነው በተኛንበት ግብፅ ሀገራችንን ተቆጣጥራ ጧት በየበራፋችን ላይ የግብፅ ሰንደቅ ዓላማ ተሰቅሎ እንዳናይ ነበር እንጅ የራሳችን ወገኖች በዘረኝነት ተነስተው የስም ዝርዝር እያነበቡ ያርዱናል ብለን አልነበረም

ከሖራ ሀይቅ ተጎትቶ የክርስትና ሀይማኖት የመስቀል በዓል በሚከበርበት መስቀል አደባባይ ላይ እንዲከበር በተደረገው የኢሬቻ አምልኮ ላይ ነፍጠኛውን ሠበርን ብለው የፎከሩት “ጀግናው” የኦሮሚያው ፕሬዚዳንት አቶ ሺመልስ አብዲሳ በእርሳቸው ግዛት ይህ ሁሉ ግፍ  ለሰዓታት ሲፈፀም ያልሰማሁት ለቅሶ ተቀምጬ ስለነበር ነው ይሉን ይሆን? አቶ ሺመልስ አብዲሣ ወንድማችን  እያሉ ሲያንቆለጳጵሱት ከነበረው ሰው ጋር የቀብር ሥነ -ሥርዓቱን እንዴት የምኒልክን ሃውልት አንስቶ ስለሚቀበርበት ሁኔታ ስትራቴጂ እየነደፉ ጊዜ አጥተው ይሆን?  

ይህ የዘር ማጥፋት (Genocide) ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ እስከታች ያሉ ሃላፊዎችና ሹማምንቶችን የሚያስጠይቅ ስለሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መልስ ሊሰጥበት ይገባል። በቴለቪዥን መስኮት ሰልጥነው ሲመረቁ ያየናቸው የኦሮሚያ ዩ ኃይል ኮማንዶዎች ሃላፊነትና ተግባር መገለፅና በኢትዮጵያዊነታቸው ላይ ያላቸው ዕምነት መጣራት ይኖርበታል።

የአብይ መንግሥት ከሚታማባቸው አንዱ በኦሮሞ አክራሪዎች ላይ ቁርጥ ያለ አቋም ማጣቱና እንደ ፖለቲካ ካርድ መጠቀሙ ነው። በአንድ እጁ የኦሮሞ ፅንፈኞችን በሌላው የትግራይ አውሬዎችን አቅፎ በመደመር ፍልስፍና ነው ኢትዮጵያን የምመራው ማለቱ የቀድሞ የሊቢያው መሪ ኮሎኔል ጋዳፊበግራ እጁ የካርል ማርክስን ዳስ ካፒታል በቀኝ እጁ ቁራን ጨብጦ ሊቢያን በአረንጓዴው መጽሐፌ (Green Book) ወይም ኪታብ አል ሂዳር ነው የምመራው ሲል ከነበረው የተለየ አይደለም።

አለመታደል ሆኖ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፈቅዶ የመረጠው መሪ ኖሮት አያውቅም። ዶ/ር አብይ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ሕዝባዊ ድጋፍ ያገኙበትን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ተግባሮችን ቢያከናውኑም የሕዝቡን ጩኸት ግን ለማዳመጥ ፈቃደኛ አልሆኑም። ይሁን እንጅ እኛ አሁንም ድምፃችን ይሰማ እያልን ከመጮህ አላቆምንም፤ አናቆምም! እንዲያውም የራሳቸውን መደመር የሚል ፍልስፍና ጭነው በመንፈስ ሀገሪቱን ለመምራት ሲጥሩ ነው የሚታዩት። ሕዝቡ ሕግ ይከበር በሕግና በሕግ እንተዳደር ሲል የታፈነ ሕዝብ ነው እስቲ እንደፈለገ ይሁን ብለን ነው የሚል ፈሊጥ አምጥተው በኦሮሞ አክራሪዎች ቅስቀሳ መተኪያ የሌላቸው ዜጎች በከተማና በየገጠሩ በጭካኔ እንዲረግፉ ሆነዋል። “በእንቁላሉ ጊዜ በቀጣሺኝ” እንዳለው ባለጌ ልጅ በጊዜው ሁሉም በሥርዓት እንዲመራ ቢደረግ ሀገሪቱ የማፊያ መፈልፈያ ባልሆነች ነበር።

“Be peaceful, be courteous, obey the law, respect everyone, but if someone put his hands on you, send him to the cemetery.”

Malcom X

የኢትዮጵያ ሕዝብ ታጋሽነቱ አልቋል፤ ትዕግሥቱ ሞልቶ እየፈሰሰ ነው፤ ከዚህ በኋላ ወደ እርስ በእርስ ግጭት አምርተን ሀገሪቱ የበለጠ መጨራረስ ውስጥ እንገባ ያስፈራል። አሁን ከዘር ፅዳት ወደ ሃይማኖት ግጭት እየገባን ነው። ይህ ደግሞ እንደ ዘር ፍጅቱ በኢትዮጵያ ክልል ብቻ ተወስኖ የሚካሄድ ፍጅት ሳይሆን ድንበር ተሻጋሪ መዘዝ አለውና አደገኛነቱ የጎላ ነው።

ዶ/ር አቢይና መንግሥታቸው ሕግ ማስከበር ካልቻሉ ቦታቸውን ችሎታ ላለው ቢለቁ ያስከብራቸዋል። ኢትዮጵያ በእኩልነት የሚያስተዳድራት ጠንካራ መሪ እንጅ በቂ ፓስተሮች ስላሏት ተጨማሪ ጎበዝ ሰባኪ አያስፈልጋትም። ኢትዮጵያ የምትተዳደረው በዘመናዊ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ሕግ እንጅ በኢሰብአዊው፣ በኋላ ቀሩ ያረጀ ያፈጀ በማይመጥናት ብዙ በሚለፈለፍበትና በሚጮህበት የገዳ ሕግ አይደለም።

ስለአባ ገዳዎች እናውራ ከተባለ ከኋላቸው ብዙ ጉድ አለ። ለምሣሌ የአባገዳዎች አውራ የሆነው ድንቁ ደያስ አባት በመላው ምሥራቅ ሸዋ ታወቁ ባለ አውሊያ ናቸው። የድንቁ የሀብት መነሻ ከሰፊው የኦሮሚያ ሕዝብ በጥቅንቆላ ማጭበርበር የተገኘ ነው። እንግዲህ ቃልቻ ደያስ ማለት ሌው ታምራት ገለታ መሆናቸው ነው። ድንቁ ደያስ ከዘራፊ ወያኔዎች ጋር በነበረው የጥቅም ግንኙነት ከደሃው የኦሮሞ ሕዝብ መሬት እየነጠቀ ለልማት መዋዕለንዋያቸውን በሀገር ውስለማፍሰስ ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ ኢትዮጵያውያን ሳይቀር በማጭበርበር የታወቀ ዲታ ሊሆን ችሏል። የዝነኛው የኦሮሚኛ ዘፋኝ የቀመር የሱፍን ሀብት አጭበርብሮ ከወሰደ በኋላ ብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር የመንግሥት ግብር ሳይከፍል ከሀገር ኮብልሎ ወጥቷል። ድንቁ ያላግባብ ገበሬውን አፈናቅሎ ባስፋፋው ሶደሬ ሪርት የእነጃዋር ቡድን እየተሰበሰበ የሽብር ሤራውን ያቀናብር እንደነበረ ይታወቃል። የሀጫሉን መገደል ተከትሎ ሌሎች አባገዳዎች የሽብር ተግባር ውስጥ ተሳታፊ በመሆን በቁጥጥር ሥር ውለዋል። እንግዲህ ብዙ የሚውራላቸው አባገዳዎች እነዚህ ናቸው። በሬ እያረዱ ብርንዶ ከመብላት ውጭ ምንም መይፈይዱ አባ ገዳዎች ሳይሆን በግብር ስማቸው አባ ገዳይ መባል ሚገባቸው ከበርቴ ሸንጋዮች ወንጀለኞችና ነፍሰ ገዳዮችን መለማመጥ ይቁም።በሀገሪቱ የተካሄደው የዘር ማጥፋት (Genocide) ነው። ገዳዮችና ጭፍሮቻቸው መዳኘት የሚኖርባቸው በገለልተኛ ፍርድ ቤት በሕግ ፍርድ እንጅ በፖለቲካ ውሳኔ በምንም ዓይነት ሊሆን አይገባም።

“የምጽፈው ሁሉ ባይተች ኖሮ መጻፌን አቆም ነበር”ቭላድሚር ኤሊች ሌኒን

ጽሑፌ ለትችት ክፍት ነው።

Shegyen@gmail.com

LEAVE A REPLY