ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ሀገር በሰለም ሚዛኗን ጠብቃ እንድጥቀጥል ከተፈለገ የሙያ ማኅበራት በገለልተኝነት መሥራት እንዳለባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አሳሰቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በተለያየ ዘርፍ በአገር ውስጥ ፈቃድ ወስደው ከሚንቀሳቀሱ የሙያ ማኅበራት ጋር ሠፊ ውይይት አካሂደዋል።
በውይይቱ የሙያ ማኅበራት ጠንካራ እንዲሆኑ ከሕግ ማሻሻል ጀምሮ ልዩ ልዩ ሥራዎች መሠራታቸውን ያስታወሱት ዶክተር ዐቢይ አሕመድ፤ በተለይም የሙያ ማኅበራቱ አዲስ አበባ ብቻ ሳይወሰኑ በሁሉም ክልሎች ሙያዊ ሥራዎችን እንዲሠሩም መልእክት አስተላልፈዋል።
መንግሥት ከመቼውም ጊዜ በላቀ የሕግ የበላይነትን ለማስከበር እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህ እውን እንዲሆን ማኅበራቱ የበኩላቸውን ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባም መክረዋል።