ፑቲን ክትባቱ በሴት ልጃቸው ላይ ለውጥ ማምጣቱን አረጋገጡ፤ የWHO ምላሽ ይጠበቃል

ፑቲን ክትባቱ በሴት ልጃቸው ላይ ለውጥ ማምጣቱን አረጋገጡ፤ የWHO ምላሽ ይጠበቃል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ሩሲያ ብዙዎች የጓጉለትንና የገዳዮን የኮሮና ቫይረስ ቀዳሚ ክትባት ማግኘቷን ይፋ አደረገች።

ከአሜሪካ ጋር ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ ያለችው ሩሲያ  በዓለማችን የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ክትባት አዘጋጅታ ማጠንቀቋን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አስታወቁ።
ይህ ተገኘ የተባለው የኮሮና ቫይረስ ቀዳሚ ክትባት በሞስኮ ጋመሌያ ኢንስቲቱዩት የተዘጋጀ ሲሆን፤ ይኸው ክትባት ዛሬ ከሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ማረጋገጫ ተሰጥቶታል።
መድኃኒቱ በክትባት ዝግጅት ላይ መታለፍ ያለባቸው ደረጃዎችን ተፈትኖ ያለፈና ውጤታማ እንደሆነ የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ፤ ሀገራቸው በቅርብ ጊዜያት የኮቪድ-19 ክትባቱን በብዛት ማምረት እንደምትጀምር ማረጋገጫ ሰጥተዋል።
 የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ክትባት የፑቲን ልጅ መውሰዷን  ያመላከተው የኢንደፔንዳት እና አርቲ ዘገባ  ፕሬዝዳንቱ ልጃቸው ክትባቱን ከወሰደች በኋላ መጠነኛ ሙቀን እንደነበራትና ከቆይታ በኋላ ግን መጠናኛ ሙቀቱ መጥፋቱን እንደመሰከሩ አስታውቋል።
በአሜሪካን መንግስት ከፍተኛ የበጀት ድጋፍ የሚንቀሳቀሰው የአለማቀፉ ጤና ድርጅት WHO ክትባቱን ይፈቅድ ይሆን የሚለው ዋነኛ ጥያቄ ምላሽ እየተጠበቀ ነው።

LEAVE A REPLY