ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በከፍተኛ ሽብርተኝነትና የሰዎች ሕይወት መጥፋት የተከሰሱት እነ አቶ ጃዋር መሀመድ “ዳኛ ይቀየርልን” ሲሉ ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ሆነ። ሽብርና እልቂት ናፋቂው ፖለቲከኛ ዳኛው ከመዝገባችን ይነሳልን ሲል ጥያቄ ያቀረበው ሰኞ ነሀሴ 4 ቀን ነበር።
ጃዋር መሐመድና ግብረ አበሮቹ ያቀረቡትን ጥያቄ የተመለከተው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዳዮን መርምሮ ብይን ሰጥቷል፡፡
አቤቱታው በማስረጃ የተደገፈ አይደለም በሚል የእነ ጃዋርን ጥያቄያቸውን ውድቅ ያደረገው ፍርድ ቤቱ፤
በዚህ መሠረት ችሎቱ ከዚህ በፊት በነበረው ዳኛ መታየቱ የሚቀጥል እንደሆነም አረጋግጧል።
በእነ አቶ ጃዋር መዝገብ 14 ሰዎች በዛሬው እለት ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፤ ዳዊት አብደታ የተባለው ተጠርጣሪ ግን በኮሮና በመጠርጠሩ በችሎት አልተገኘም።