ኢትዮጵያዊው የሒሳብ ሊቅ ፕ/ር ሙላቱ ለማ ከዶናልድ ትራምፕ እጅ ፕሬዝዳንታዊ ሽልማት ተቀበሉ

ኢትዮጵያዊው የሒሳብ ሊቅ ፕ/ር ሙላቱ ለማ ከዶናልድ ትራምፕ እጅ ፕሬዝዳንታዊ ሽልማት ተቀበሉ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በአሜሪካ ሳቫና ስቴት ዩኒቨርስቲ የሒሳብ ሊቅ ሆነው በፕሮፌሰርነት ማእረግ በማስተማር ላይ ያሉት ዶክተር ሙላቱ ለማ ከፍተኛውን ፕሬዝዳንታዊ ሽልማት ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እጅ መቀበላቸው ተሰማ።

ፕሮፌሰሩ ሽልማቱን የተቀበሉት በሒሳብ፣ ሳይንስ እና ምህንድስና ዘርፍ ባበረከቱት ምሁራዊ የማስተማር አስተዋፅዖ መሆኑ ታውቋል።
የመጀመሪያና የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን በ1970ዎቹ በኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በአፕላይድ ማቲማቲክስ ያጠናቀቁት ፕሮፌሰር ሙላቱ ወደ አሜሪካ ካቀኑ በኋላ ከኬንት ዩኒቨርስቲ በፒዩር ማቲማቲክስ ትምህርት ዘርፍ የሁለተኛ ዲግሪ (ማስተርስ) እና የሦስተኛ ዲግሪ (ፒ.ኤች.ዲ) ተመርቀዋል፡፡
በሳቫና ዩኒቨርስቲ በነበራቸው ለ25 ዓመታት የዘለቀ የማስተማር ቆይታ ከአንድ መቶ የሚልቁ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን ያበረከቱ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ በ2011 በስማቸው የተሰየመ የቁጥር ስርዓትን ለዘርፉ ያስተዋወቁ ታላቅ ምሁር  መሆናቸውም ይነገርላቸዋል።
 ለቀጣዩ የአሜሪካ የፈጠራ ሥራዎች ትውልድ መሰረትን ለመጣል ችለዋል የተባሉ ሌሎች 12 ምሁራን እና 3 ተቋማት  የዘንድሮ ሽልማት አሸናፊ በመሆን ከፕሬዝዳንት ትራምፕ እጅ ሽልማታቸውን መቀበላቸው ተረጋግጧል።

LEAVE A REPLY