ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተከትሎ ኅብረተሰቡ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ወይም ማሰክ አጠቃቀምን ለማሳደግ ዓላማ ያደረገው ንቅናቄ ተጀመረ።
ንቅናቄው እየጨመረ የመጣውን የኮሮና ወረርሽኝ ለመካለከል ከፍተኛ ሚና እንዳለው የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።
ሁሉም ኅብረተሰብ እጆቹን ከመታጠብ እና አካላዊ ርቀትን ከመጠበቅ በተጨማሪ፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛዎችን በአግባቡ እንዲጠቀምም ሚኒስትሯ መልእክት አስተላልፈዋል።
“ማስክ ኢትዮጵያ” በተሰኘው ንቅናቄ ሽልማት ያላቸው የተለያዩ ውደድሮች መዘጋጀታቸውን የተናገሩት የጤና ሚኒስትሯ ፤ የፎቶግራፍ ውድድር፣ የቪዲዮ እና የሬዲዮ ማስታወቂያ መወዳደሪያ መንገዶቹ መሆኑንም ገልጸዋል።
እስከ ነሃሴ 18 ቀን 2012 ዓ.ም በሚቆየው በዚህ ውድድር ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ግለሰቦች ሥራዎቻቸውን በMaskEthiopia@g
mail.com ላይ መላክ እንደሚችሉም ታውቋል።