ሀብታቸውን ያላስመዘገቡ ባለሥልጣናት ዝርዝር ነገ ለፖሊስ ይተላለፋል ተባለ

ሀብታቸውን ያላስመዘገቡ ባለሥልጣናት ዝርዝር ነገ ለፖሊስ ይተላለፋል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ሀብታቸውን ያላስመዘገቡ የፌደራል መንግሥቱ ባለሥልጣናትን ስም ዝርዝር ከነገ ጀምሮ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አሳልፎ ለመስጠት ዝግጅቱን ማጠናቁን የፌደራል ሥነ ምግባርና ፀረ- ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።

ተቋሙ እዚህ ውሳኔ ላይ ከመድረሱ በፊት ባለሥልጣናቱን በተለያያ ጊዜ ህጉን ተከትለው ምዝገባ እንዲያደርጉ ከመጠየቅና ከመለማመጥ ባሻገር በቅርብ ሰዎቻቸው ጭምር አማላጅ እስከመላክ መድረሱን ገልጿል።
አብዛኛዎቹ ከፍተኛ የሥራ ሓላፊዎችሚኒስትርና ሚኒስትር ዴኤታዎች ኮሚሽኑ ባስቀመጠው ጊዜ ገደብ ሀብታቸውን እስከ ሐምሌ 30 ቀን ድረስ ቢያስመዘግቡም በአንጻሩ በጣት የሚቆጠሩ ሚኒስትርና ሚኒስትር ዴኤታዎች በተደጋጋሚ ሀብታቸውን እንዲያስመዘግቡ በፌደራል ሥነ ምግባርና ፀረ ኮሚሽን ቢጠየቁም ፍቃደኛ ባለመሆናቸው፤ ህግን የማስከበር ሥራ ለመሥራት ኮሚሽኑ አስፈላጊ አባሪ ሰነዶችን አዘጋጅቶ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ እንዲሁም በግልባጭ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤትና ለጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ጽ/ቤት ለማስገባት መወሰኑም ታውቋል።
ኮሚሽኑ ሀብታቸውን ለማስመዝገብ ፈቃደኛ ያልሆኑ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናትን፣ ሓላፊነቱን ለመወጣት በተደጋጋሚ በደብዳቤ፣ በስልክ፣ በአጭር ጽሑፍ መልእክት፣ ከማሳወቁና በአካል ከማሻገሩ ባሻገር  በሚቀርቧቸው የሥራ ባልደረቦቻቸው ቢያስጠይቅና አማላጅ ቢልክም ምላሽ  አለማግኘቱን ይፋ አድርጓል።

LEAVE A REPLY