መድረክ፣ ኦነግ፣ አረናና ሲአን “ትብብር” የተሰኘ ግንባር ለመመሥረት ምርጫ ቦርድን ጠየቁ

መድረክ፣ ኦነግ፣ አረናና ሲአን “ትብብር” የተሰኘ ግንባር ለመመሥረት ምርጫ ቦርድን ጠየቁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት(መድረክ) በውስጡ ከያዛቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በጋራ ለመሥራት ሌሎች ተጨማሪ አምስት የፖለቲካ ድርጅቶች በጋራ የሚመሰርቱት ግንባር “ትብብር” ን ለመመሥረት ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፈቃድ ለማግኘት የስምምነት ሰነድ ማስገባታቸው ታወቀ።

ትብብሩን ለመመሥረት የተስማሙት ፓርቲዎች የመድረክ ግንባር አባል ድርጅቶች በመድረክ ስም፣ እንዲሁም የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)፣ የአገው ብሔራዊ ሸንጎ፣ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ)፣ የከፋ አረንጓዴ ፓርቲ እና ሞቻ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ እንደሆኑ የመድረክ ጸሐፊ ደስታ ዲንካ ተናግረዋል።
በመድረክ ውስጥ ታቅፈው ከሚገኙ የፖለቲካ ድርጅቶች  የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)፣ ዓረና ትግራይ ለዲሞክራሲያዊ ፍትህ ፓርቲ፣ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን)፣ የኢትዮ ሶሻል ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኢሶዴፓ ናቸው ትብብርን ለመመሥረት እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት።

LEAVE A REPLY