ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ከነገ ነሐሴ 12 ቀን ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ ሁለት ሰዐት እስከ ረፋዱ አራት ሰዐት ድረስ በከፍተኛ የኤሌክትሪክ ተሸካሚ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን ሲባል የኃይል አቅርቦት እንደሚቋረጥ ተሰማ።
ነገ የኃይል አቅርቦቱ ከሚቋረጥባቸው አካቢዎች መካከል፤ በአዲሱ ገበያ፣ በሰሜን ማዘጋጃ፣ በላዛሪስት ትምህርት ቤት፣ በሩፋኤል ቤተ-ክርስትያን፣ በገርጂ ኮንደሚኒየም በኢምፔሪያል ሆቴል፣ በገርጂ ጤና ጣቢያ፣ በዳችያ ቀለም፣ በገርጂ አንበሳ ጋራዥ እና አካባቢዎቻቸው መብራት አይኖርም ተብሏል።
በተጨማሪም ቦሌ መድኃኒዓለም ቤተ-ክርስቲያን፣ በአያት ሆስፒታል፣ በብራስ ሆስፒታል፣ በሚሊኒየም አዳራሽ፣ በቦሌ ሚኒ፣ በጎላጎል፣ በቺቺኒያ፣ በቦሌ ሚሊኒየም፣ በሰሚት ኮንደሚኒየም እስከ በፍየል ቤት፣በጊዮርጊስ ቤተ-ክርስትያን እና አካባቢዎቻቸው የኤሌክትሪክ አገልግሎት በእደሳው ምክንያት ይቋረጣል ተብሏል።
በተመሳሳይ ረቡዕ ነሐሴ 13 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ድረስ፤ በዘነበወርቅ ቶታል፣ በአለርት ሆፒታል፣ በገርጂ ዩኒቲ ኮሌጅ፣ በቦሌ ሆምስ፣ በቦሌ ሲቪል አቬሽን፣ በጎሮ አለማየሁ ህንፃ፣ በጃክሮስ፣ በተወካዮች ምክር ቤት እና አካባቢዎቻቸው፣ እንዲሁም በራስ ደስታ ሆስፒታል፣ በእየሩሳሌም ሆቴል፣ በእምቢልታ ሆቴል፣ በእንቁላል ፋብሪካ እና አካባቢዎቻቸው መብራት እንደማይኖር ባለሥልጣን መ/ቤቱ አስታውቋልተ
ሀሙስ ነሐሴ 14 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ረፋዱ 4፡00 ድረስ፤ በኢትዮ-ፕላስቲክ፣ የነገው ሰው ትምህርት ቤት፣ በ17/24 ታክሲ ማዞርያ፣ በአዲሱ የወጣቶች ማዕከል ስታዲየም እና አካባቢዎቻቸው፣ በተጨማሪም ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ በቦሌ መድኃኒአለም ቤተ-ክርስትያን፣ በአያት ሆስፒታል፣ በብራስ ሆስፒታል፣ በሚሊኒየም አዳራሽ፣ በቦሌ ሚኒ እና አካባቢዎቻቸው የመብራት አገልግሎት የማይኖሮ በመሆኑ ኅብረተሰቡ ከወዲሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ባለሥልጣን መ/ቤቱ አሳስቧል።