ልደቱ አያሌው ተስፋ እንደቆረጡና ምናልባትም ከሁለት ዓመት በኋላ ሊፈቱ እንደሚይፈችሉ ተናገሩ

ልደቱ አያሌው ተስፋ እንደቆረጡና ምናልባትም ከሁለት ዓመት በኋላ ሊፈቱ እንደሚይፈችሉ ተናገሩ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– እስካሁን ጥብቅና የሚቆምላቸው አጥተው በራሳቸው ሲከራከሩ የቆዩት አቶ ልደቱ፤ ዛሬ በጠበቃ እንደተከራከሩ ታወቀ።

“አቶ ልደቱ ጠበቃ ማግኘት እንዳልቻሉ በየሚዲያው ከገለፅን በኋላ ባለፈው ሳምንት ኦሮሚያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ኦሮምኛ ተናጋሪ ጠበቆች በነፃ እንቆምልሃለን ባሉት መሰረት ዛሬ የተከራከሩት ከአንድ ጠበቃ ጋር እየተመካከሩ ነው” ነው ያሉት የኢዴፓ ሊቀመንበር አቶ አዳነ፤ አቶ ልደቱ በሚሰጠው ቀጠሮ ተስፋ የቆረጡ መሆኑና ” ድንገት ከምርጫው በኋላ፣ ምናልባትም ከሁለት ዓመት በኋላ ነው ልለቀቅ የምችለው፣ እስከ ሁለት ዓመት ራሴን አዘጋጅቼ ነው ያለሁት” ሲሉ የነገሯቸው መሆኑንም ገልጸዋል።
ልደቱ አያሌው የጤና ሁኔታቸው አሳሳቢ እንደሆነና ዛሬ ፍርድ ቤት ከገቡ ጀምሮ ነስር በተደጋጋሚ እያስቸገራቸው እንደነበር የተናገሩት አቶ አዳነ፤ ሕክምና እንዲያደርጉ የሚያሳይ በቂ ማስረጃ ቢኖርም፣ ፍርድ ቤቱ ባለመፍቀዱ አቶ ልደቱ “ዛሬ የተፈረደብኝን የሞት ፍርድ የተፈረደብኝ ያህል ነው የምቆጥረው” ማለታቸውንም ይፋ አድርገዋል።
 የሚመጣውን ውጤት ከመጠበቅ ውጭ በፍርድ ሂደቱ እኛም ተስፋ ቆርጠናል ያሉት የኢዴፓው ሊቀመንበር፣
እስሩ ፖለቲካዊ ነው ከማለታቸው ባሻገር፣ ጉዳዩን በንግግር ለመፍታት ከዚህ በፊት ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና ለምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ማስገባታቸውንና ለመወያየት ጥረት ያደረጉ ቢሆንም፤  ፍርድ ቤት የያዘው ጉዳይ ስለሆነ ጣልቃ መግባት እንደማይችሉ የነገሯቸው መሆኑን ለቢቢሲ አስረድተዋል።
አሁን ላይ በደብረዘይት ከተማ በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ልደቱ አያሌው ያሉበት የጤንነት ሁኔታ አሳሳቢ በመሆኑ፤ ኢዴፓ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ደብዳቤ ለመጻፍ መዘጋጀቱም ተሰምቷል።

LEAVE A REPLY