ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለመጀመሪያ ጊዜ ተገቢ ተሿሚ አገኘ፤ አዳነች አቤቤ ተነሱ

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለመጀመሪያ ጊዜ ተገቢ ተሿሚ አገኘ፤ አዳነች አቤቤ ተነሱ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የነበሩትና የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን መ/ቤትን በአጭር ጊዜ ውስጥ በተረኛ ብሔርተኝነት ያጥለቀለቁት አዳነች አቤቤ ከሓላፊነታቸው ተነሱ።

በአንጻሩ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለመጀመሪያ ጊዜ ትክክለኛ ሙያተኛና የፓርቲ አባል ያልሆነ ሰው በሓላፊነት ተሹሞበታል።
ከለውጡ ማግስት አንስቶ የተሾሙት ሁለቱም ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጎች (አቶ ብርሃኑና ወ/ሮ አዳነች) ሹመቱን ከፖለቲካ ፓርቲ አባልነታቸው ጋር ያገኙት ከመሆኑ ባሻገር በአቋም ረገድም የወገንተኝነት ስሜት የሚንጸባረቅባቸው እንደሆኑ ይነገራል።
ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሆኖ የተሾመው ወጣቱ የሕግ ባለሙያ  ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቴዎስ፤ ለቦታው ትክክለኛ ሰው እንደሆነ ብዙዎች ተስማምተውበታል።
ከፓርቲ አባልነት ውጭ በሆነ መንገድ በሙያ ብቃት ወደ ሥልጣን የመጣው ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ አቶ ብርሃኑም ሆነ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በሥልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት የሕግ አግባብን የተከተሉ ትክክለኛ ሥራዎችን ሢመራና ሲያስፈጽም የነበረው እርሱ መሆኑን ለመ/ቤቱ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ይናገራሉ።

LEAVE A REPLY