የገቢዎች ሚኒስቴር በባለፈው በጀት ዓመት 233 ነጥብ 7 ቢሊዮን አገኘሁ አለ

የገቢዎች ሚኒስቴር በባለፈው በጀት ዓመት 233 ነጥብ 7 ቢሊዮን አገኘሁ አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የገቢዎች ሚኒስቴር ባለፈው በጀት ዓመት 233 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ገቢ አግኝቻለሁ አለ።

የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው የተቋሙን ያለፈው በጀት አፈፃፀም እንዲሁም ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስመልከት መግለጫ የሰጡ ሲሆን፤ ሚኒስቴሩ ባለፈው በጀት ዓመት 270 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ፣ 233 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 86 ነጥብ 5 በመቶ አሳክቷል ብለዋል።
ይህ ገንዘብከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ17 በመቶ ብልጫ እንዳለውም ታውቋል።
በመግለጫው መሠረት ከሀገር ውስጥ ገቢ 128 ቢሊዮን ወይም 84 በመቶ፣ ከውጭ ንግድ ጉምሩክ 104 ነጥብ 9 ቢሊዮን፣ ከሎተሪ 152 ሚሊየን ገቢ መገኘቱን ገንዘብ መሰብሰብ ተችሏል።
በአመራርና ሠራተኛው ከሌሎች አጋር አካላት ጋር ተግባብቶ በመሥራት፣ የቴክኖሎጂ (e-tax አጠቃቀም፣ የህግ ማዕቀፍ ማሻሻል፣ የታሪፍ ማሻሻያ፣ ህግና ስርዓት ማስከበር፣ ከግብር ከፋዮች ዕውቅና መስጠት እና የዋጋ ትመና አሰራር ማሻሻያ የማድረግ ሥራም ተከናውኗል።

LEAVE A REPLY