ጊዜው ያለፈባቸው በርካታ ምግቦች በአምስቱም ኬላ ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡ ሲሉ ተያዙ

ጊዜው ያለፈባቸው በርካታ ምግቦች በአምስቱም ኬላ ወደ ኢትዮጵያ ሊገቡ ሲሉ ተያዙ

[ File # csp6017057, License # 1298625 ] Licensed through http://www.canstockphoto.com in accordance with the End User License Agreement (http://www.canstockphoto.com/legal.php) (c) Can Stock Photo Inc. / Mhayashi

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን በሐምሌ ወር ብቻ በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገኙ አምስቱ መግቢያና መውጫ ኬላዎች ያደረገውን ቁጥጥር ተከትሎ ሕገ ወጥ የምግብ ምርቶች እና ጥሬ እቃዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገለጸ።

በጉዞ ወቅት የተበላሹ፣ የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው፣ እንዲሁም አስገዳጅ የገላጭ ጽሑፍ ያላሟሉ ከ227 ነጥብ 64 ቶን በላይ ምግብና የምግብ ጥሬ ዕቃ ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው ጥቅም ላይ እንዳይውሉ መደረጉንም ባለሥልጣኑ ይፋ አድርጓል።
ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመሆን በመግቢያና መውጫ ኬላዎች ላይ ባደረገው ቁጥጥር፤ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ የተደረጉት ምርቶች ኅብረተሰቡ በዕለት ተዕለት ኑሮ በስፋት የሚጠቀምባቸው መሆኑም ታውቋል።
በመረጃው መሠረት የተበላሸ የምግብ ዘይትና ወተት፣ የተበላሸ የቲማቲም ድልህ፣ አስገዳጅ የገላጭ ጽሑፍ መስፈርትን ያላሟላ የምግብ ጥሬ ዕቃ ከተያዙትና ከተወገዱት ምርቶች መሀል እንደሚገኝበት ከኢትዮጵያ የምግብ መድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታውቋል።

LEAVE A REPLY