ለህዳሴው ግድብ በአንድ ወር ውስጥ ከ116 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ

ለህዳሴው ግድብ በአንድ ወር ውስጥ ከ116 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያው ዙር ውሃ ሙሌት መከናወኑን ተከትሎ በአንድ ወር  ውስጥ ብቻ ከ116 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ  ተሰማ።

የግድቡ ግንባታ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ከግድቡ የመጀመሪያ ዙር ውሃ ሙሌት በኋላ ድጋፉ ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቁሞ፤ ከሙሌቱ በኋላ ከ116 ሚሊዮን ብር በላይ ለግንባታው ድጋፍ ሰብስቢያለሁ ብሏል።
የጽሕፈት ቤቱ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሃይሉ አብርሃም ለግድቡ ግንባታ ስኬት የመንግሥትና የግል ተቋማት፣ ባንኮችና ኢንሹራንሶች፣ የዳያስፖራው ማኅበረሰብን ጨምሮ በሁሉም ማኅበረሰብ ክፍሎች ዘንድ ከፍተኛ የሆነ መነቃቃት መስተዋሉን አስረድቷል።
በሐምሌ ወር  ከ8100 “A” አጭር የጽሑፍ መልዕክት ገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ከ11 ሚሊዮን 271 ሺኅ ብር በላይ ገቢ የተገኘ ሲሆን፤ በዚሁ ወር ከቦንድ ግዢ እና ከስጦታ ደግሞ 105 ሚሊዮን 201 ሺኅ 874 ብር መሰብሰቡን የገለጹት አቶ ኃይሉ፤ በዚህም በአጠቃላይ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ብቻ 116 ሚሊዮን 473 ሺኅ 348 ብር ገቢ እንዲገኝ እድል ፈጥሯል በማለት ተናግረዋል።

LEAVE A REPLY