ሁለት ሴቶች በጋምቤላ ተደብድበው ሕይወታቸው ማለፉ ተረጋገጠ

ሁለት ሴቶች በጋምቤላ ተደብድበው ሕይወታቸው ማለፉ ተረጋገጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በጋምቤላ ክልል ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች ባደረሱት ጥቃት የኹለት ሴቶች መገደላቸው ተሰማ።

ከቀናት በፊት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኹከትና ግጭት እየታየበት በሚገኘው የጋምቤላ ክልል ፤ ሁሉት ሴቶች ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች በደረሰባቸው  ጥቃት ሳቢያ ህይወታቸው ሊያልፍ እንደቻለ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ማረጋገጫ ሰጥቷል።
የጋምቤላ ክልል ሰላምና ፀጥታ ዘርፍ ምክትል ሓላፊ ኦቶው ኦኮት፤ ጥቃት አድራሾቹ  ግለሰቦች ሰሞኑን በኹለት ሴቶች ላይ በፈፀሙት ጥቃት ሳቢያ ህይወታቸው ማለፉን ተረድተናል ብለዋል።
በሴቶቹ ላይ ዘግናኝ ድብደባ የፈጸሙት ጥቃት አድራሾች በቁጥጥር ሥር የዋሉ በመሆኑ  ክስ እንዲመሰረትባቸው እየተሠራ እንደሆነም ታውቋል።

LEAVE A REPLY