ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የተለያዮ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን በመገንባት ላይ የተጠመደው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት በቀጣዮቹ ዓመታት በመላ ሀገሪቱ ከፍተኛ የሚባልለትን የመንገድ ግንባታ እንደሚያከናውን ተነገረ።
እንደመረጃው ከሆነ በኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ዐሥር ዓመታት ከ225 ሺኅ ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ ለመገንባት መታቀዱን ባለሥልጣን መ/ቤቱ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የሕዘብ ግንኙነት ሓላፊ አቶ ሳምሶን ወንድሙ ሀገሪቱ በሚቀጥሉት ዐሥርት አመታት ምንም ዓይነት የጸጥታም ሆነ ሌሎች ችግሮች ቢኖሩም ከ225 ሺኅ ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ ለመገንባት በመንግሥት ደረጃ እቅድ መያዙን ይፋ አድርገዋል።
የታሰቡትን መንገዶች ለመገንባት ከፍተኛ የሆኑ ችግሮች መኖራቸው ባያጠራጥርም ፤ እቅዱ ያንን ታሳቢ ያደረገ በመሆኑ መልማት ያለባቸው የሀገሪቱ ክልሎች እንደሚለሙና የጸጥታ ችግሮች የብልፅግና ጉዞውን እንደማያደናቅፉት አረጋግጠዋል።