ጋዜጠኛ ያሲን ጁማ ከእስር ቢለቀቅም ኮሮና ስለተገኘበት ለይቶ ማቆያ እንዲገባ ተደረገ

ጋዜጠኛ ያሲን ጁማ ከእስር ቢለቀቅም ኮሮና ስለተገኘበት ለይቶ ማቆያ እንዲገባ ተደረገ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በጃዋር መኖሪያ ቤት የተያዘውና በአዲስ አበባም ሆነ በኢትዮጵያ ለመሥራት ፍቃድ የሌለው ኬንያዊው ጋዜጠኛ ያሲን ጁማ ከእስር ተለቀቀ።

ጋዜጠኛው ከእስር ቢፈታም በኮሮና ቫይረስ የተያዘ መሆኑ በመረጋገጡ የኮሮና ቫይረስ ህሙማን ለይቶ ማቆያ እንዲገባ መደረጊ ተረጋግጧል።
የሙዚቀኛ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በአቶ ጃዋር መሐመድ መኖሪያ ቤት በቁጥጥር ስር ከዋሉት ተጠርጣሪዎች መካከል አንዱ የሆነው ከእስር ተፈቺው ኬንያዊ ጋዜጠኛ፤ በሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የእስር ቆይታው በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተገልጿል።
ጉዳዮን አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጠው የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፤ ጋዜጠኛው የተፈታው በኢትዮጵያ የሚገኘው የአገራቸው ኤምባሲ ጣልቃ ገብቶ እንደሆነ ጠቁሞ፤ በኢትዮጵያ የሚገኘው የኬንያ ኤምባሲ የጋዜጠኛውን እስር በመቃወም ተደጋጋሚ ደብዳቤዎች መጻፉን ጭምር ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አብራርቷል።
ከቀናት በፊት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ነሐሴ 1 በዋለው ችሎት ያሲን ጁማን ጨምሮ የ11 ሰዎች የዋስትና መብት ተከብሮላቸው በዋስ እንዲወጡ ቢወስንም፤ ፖሊስ ያሲን ጁማን በሌላ የወንጀል ደርጊት ጠርጥሬዋለሁ ሲል በእስር እንዲቆይ ያደረገው መሆኑ አይዘነጋም።

LEAVE A REPLY