የትግራይ ክልል የመራጮች ምዝገባ ዛሬ ጠዋት ተጀመረ

የትግራይ ክልል የመራጮች ምዝገባ ዛሬ ጠዋት ተጀመረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና በአምባገነኑ ህወሓት ፈላጭ ቆራጭነት ከህግ አግባብ ውጭ በምትተዳደረው የትግራይ ክልል የመራጮች ምዝገባ ዛሬ መጀመሩ ተሰማ።

ከሳምንታት በፊት በህወሓት ቱባ ባለሥልጣናት በተመለመሉ ግለሰቦች የተቋቋመው የምርጫ አስፈጻሚ ኮሚሽን ፤ በክልሉ ለሚካሄደው 6ኛው ክልላዊ ምርጫ ዛሬ  ነሀሴ 15/2012 ጠዋት የመራጮች ምዝገባ መጀመሩን ይፋ አድርጓል።
የትግራይ ክልል የምርጫ ኮሚሽን ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ክልላዊ ምርጫው በጷግሜ 04/2012 ዓ.ም የሚከናወን ሲሆን፤ በትግራይ ክልል የመራጮች ምዝገባም እስከ ነሐሴ 18 ድረስ ለሦስት ቀናት ይቆያል።

LEAVE A REPLY