ወ/ሮ ስህን ሚካኤል አሊ

ወ/ሮ ስህን ሚካኤል አሊ

የወሎው ራስ ሚካኤል አሊ ልጅ ፤

የልጅ እያሡ ሚካኤል እህት ፤
የአምባሠሉ ገዥ የጃንጥራር አስፋው ሚሥት ፤
እቴጌ መነን አስፋው እናት (የቀ/ኃይለሥላሴ ሚሥት)
የመጀመሪያዋ የደሴ የወ/ሮ ስህን ት/ቤት ተማሪ …

የወ/ሮ ሰህን ትምህርት ቤት ሲነሳ በ1965ዓ.ም አካባቢ የነበረውን የኢትዮጵያ የተማሪዎች ንቅናቄ አብሮ ይነሳል።በኢትዮጵያ ፖለቲካና የለውጥ አብዮት ውስጥ ከፍተኛ ሚና የነበራቸው ግለሰቦች የፈለቁትም ከዚሁ ት/ቤት ነው።

ደሴ ውስጥ የሚገኘው ወ/ሮ ስህን ት/ቤት በኢትዮጵያየ የመጀመሪያው አጠቃላይ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው። በእጅ የያዙት ወርቅ እንደ መዳብ ይቆጠራል ነው እና ነገሩ የመጀመሪያ የሚለውን ስትመለከት ደሴ የዕውቀት ችቦ አብሪ መሆኗን አመኖ ከመቀበል ውጭ ምንም ምርጫ አይኖርህም !!!!

ትምህርት ቤቱ ስያሜውን ያገኘው በ1922 ዓ.ም በንጉስ ሚካኤል ልጅ ስህን ሚካኤል ሲሆን /ሮ ስህን የንጉሥ ሚካኤል ልጅ፣ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ አማት፣ የእቴጌ መነን አስፋው እናትና የልጅ ኢያሱ ታላቅ እህት ናቸው፡፡

የወ/ሮ ስህን የመጀመሪያው የትዳር አጋራቸው ጃንጥራር አስፋውን ነበር፡፡ በ1904 ዓ.ም ግን የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የአጎት ልጅ የሆኑትን ደጃዝማች ብሩ ኃይለማርያምን አግብተው ከወሎ ወደ ሽዋ መጡ።

ወንድማቸው ልጅ ኢያሱ በትረ-መንግሥቱን በጨበጡበት ጊዜ ደግሞ በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩትን ቢትወደድ ኃይለጊዮርጊስ ወልደሚካኤልን አገቡ፡፡

ወ/ሮ ስህን በልጃቸው በጃንጥራር ሃ/ማሪያም ቦታ ላይ “ሳላይሽ” ተብሎ ከሚጠራው ቦታ መሰረቱ እንዲጣል ከአደረጉ በኋላ 25ሺህ ማርትሬዛ ድጋፍ አድርገዋል።
ወ/ሮ ስህን በ1920ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ቢለዩም ሥራውን በኃላፊነት ይመሩት የነበሩት የጋብቻ ዝምድና የነበራቸው የከንቲባ ገብሩ ልጅ ወ/ሮ ስንዱ ገብሩ አስጨርሰውታል።

ታህሳስ 24 ቀን 1936 ዓ.ም ታትሞ ከወጣው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለመረዳት እንደሚቻለው ተመርቆ የተከፈተው ጳግሜ 4 ቀን በ1935 ዓ. ም በዋና ሥራ አስኪያጅዋ በወ/ሮ ስንዱ ገብሩ ንግግር ነበር፡፡ የምረቃውን በዓል በይፋ የከፈቱት የወ/ሮ ስህን የልጅ ልጅ የሆኑት ልዑል አልጋወራሽ አስፋ ወሰን ኃይለሥላሴ ናቸው።

በ1939 ዓ.ም ግን የስህን ሚካኤል የልጅ ልጅ አልጋወራሽ መርድ አዝማች አስፋወሰን ኃይለስላሴ የተማሪዎች ቁጥር በመጨመሩ ት/ቤቱ አሁን ወደሚገኝበት የመሰረት ድንጋይ ጥለው ድንጋይ በድንጋይ ባለአንድ ፎቅ ህንፃ እንዲሰራና እንዲሸጋገር ተደርጎ እስከ 1949 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ከ1ኛ-8ኛ ክፍል የመማር ማስተማር ሂደት ሲያከናው ቆይቷል፡፡

እንደገና የተማሪው ቁጥርም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር በተያያዘ 15 ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች ተገንብተው ከመስከርም ወር 1950 ዓ.ም ጀምሮ በእቴጌ መነን ተመርቆ በሃገራችን የመጀመሪያው አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመባል ሥራውን በ63 ተማሪዎች ቀጥሏል።

ለመጀመሪያ ጊዜ 12ኛ የጨረሱ ተማሪዎች ለመልቀቂያ ፈተና የተቀመጡት በ1953 ዓ.ም ነበር ።

በ1956 ዓ.ም. ደግሞ የ1ዐኛ ክፍልን ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች የ2 ዓመት የሙያ ሥልጠና በተለያዩ መስኮች በመውሰድ በዲኘሎማ ተመርቀዋል።

ት/ቤቱ ከቀለሙ ትምህርት ባሻገር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትን አካቶ ትምህርት በመስጠቱ በኢትዮጵያ የመጀመሪያዉ የቴክኒክና ሙያ ፣በእርሻና ተግባረዕድ የሙያ ዘርፎች ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል፡፡

1956 ዓ.ም የስህን ት/ቤት ውስጥ በ40 ተማሪዎች የሙዚቃ ባንድ ተቋቁሟል።መምህራቸው ደግሞ /ር ሮናልድ ቤል የተባለ #ሜሪካዊ እና ኢትዮጵያዊው የሙዚቃ ሰው አቶ ለማ ፈይሣ ነበሩ።

ከዚህ የሙዚቃ ት/ቤት ውስጥ ተምረው ከወጡት መካከል በሀገራችን የሙዚቃ ታሪክ ከ22 በላይ የሙዚቃ ካሴቶችን ያሳተመው “እዚያ ማዶ ጋራ፣ ያዢልኝ ቀጠሮ ፣

አይባባ ሆዴ ፣ # አይሽና፣ መልካም ልደት”በተሰኙት ተወዳጅ ዘፈኖቹ የምናውቀው አንጋፋው ድምፃዊ መስፍን አበበ የስህን ት/ቤት ውጤት ነው። ልሎችም እነ አበበ ሃይለሚካኤል፣ ተክለማሪያም ረዲ እና የተውኔት ደራሲ የነበረው ፍስሃ በላይ ይማም ይጠቀሣሉ፡:

በ1970 ዓ.ም የት/ቤቱ ስም የካቲት 66 አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሚል ስያሜ ያገኘ ሲሆን በመቀጠልም የካቲት 66 የቀለም ቴክኒክ ሙያ ት/ቤት ተባለ።

በ1984 ዓ.ም የት/ቤቱ ስም ወ/ሮ ስሂን የቀለም ቴክኒክ ሙያ ት/ቤት ተብሎ ተሰየመ ።

በ1994 ዓ.ም ወ/ሮ ስሂን ቴክኒክና ሙያ ተቋም በሚል ስያሜ በተለያዩ የስልጠና ዘርፎች በመደበኛና በማታ መርሀ ግብር ስልጠና በመስጠት በሰርተፍኬት ደረጃ ማስመረቅ ጀመረ።
በ2000 ዓ.ም ተቋሙ ከደሴ ቢዝነስና ስራ አመራር ኮሌጅ ጋር ተዋህዶ ስሙም ወ/ሮ ስሂን ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ በሚል ተቀየረ ።
በትምህርት ዘመናችሁ የነበራችሁን ትዝታ እያጣጣማችሁ

ከFB የታወሰደ

LEAVE A REPLY