ሁለተኛው ዙር የአዲስ አበባ መንደሮች የኤሌክትሪክ መቋረጥ ረቡዕ ይጀምራል ተባለ

ሁለተኛው ዙር የአዲስ አበባ መንደሮች የኤሌክትሪክ መቋረጥ ረቡዕ ይጀምራል ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በአዲስ አበባ የተለያዮ ሥፍራዎች የማቋረጡ ሂደት ከረቡዕ እለት ጀምሮ እንደሚቀጥል ታወቀ።

በቀጣዮቹ ቀናት የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎቱ የሚቋረጠው በዘርፉ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን ሲባል መሆኑም ተነግሯል።
በወጣው ፕሮግራም መሠረት ረቡዕ ነሀሴ 20 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ድረስ በመካኒሳ አቦ፣ በደሴ ሆቴል፣ በካርል አደባባይ፣ በብስራተ ገብርኤል እና አካባቢዎቻቸው፤ እንዲሁም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 8፡30 ድረስ በአድዋ ድልድይ፣ በአቧሬ፣ በቤልኤር፣ በእንደራሴ ሆቴል፣ በመለስ ፋውንዴሽን፣ በልቤ ፋና ኮንደሚኒየም፣ በካዛንችስ በከፊል፣ በላፍቶ ኢንዱስትሪ መንደር እና አካባቢዎቻቸው የኃይል አቅርቦት እንደሚቋረጥ ታውቋል።
ሐሙስ ነሀሴ 21 ቀን 2012 ዓ.ም ደግሞ ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ በኮተቤ 02፣ በደህንነት፣ በሃና ማርያም፣ በሃይሌ ጋርመንት፣ በቆጣሪ ኮንደሚኒየም፣ በኦሮሚያ ኮንደሚኒየም፣ በማንጎ ሰፈር፣ በቸራልያ ፋብሪካ፣ በገነት መናፈሻ ኮንደሚኒየም፣ በማሩ ብረታ ብረት፣ በወህኒ ቤት ጀርባ፣ በቂሊንጦ ማረምያ ቤት አካባቢ መብራት እንደማያገኙ ተሰምቷል።
አርብ ነሀሴ 22 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ድረስ በአደይ አበባ፣ በሳሪስ አዲስ ሰፈር፣ በአዋሽ ቆዳ ፋብሪካ እና አካባቢዎቻቸው፤ በመካከለኛ የኤሌክትሪክ ተሸካሚ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን ሲባል የኃይል አቅርቦት እንደሚቋረጥ ኮርፖሬሽኑ አስታውቋል።

LEAVE A REPLY