ታከለ ኡማ ለአ/አ ፖሊስ አባላት አስገነባዋለሁ ያሉት የመኖሪያ ቤት እስካሁን አልተጀመረም

ታከለ ኡማ ለአ/አ ፖሊስ አባላት አስገነባዋለሁ ያሉት የመኖሪያ ቤት እስካሁን አልተጀመረም

ኢትዮጵያ ነገ ዜና በቅርቡ ከአዲስ አበባ ከንቲባነታቸው የተነሱት ኢ/ር ታከለ ኡማ ከፍተኛ ወጪ ሊያስገነቡት የነበረው የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት መኖሪያ እስካሁን እንዳልተጀመረ ታወቀ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር ወጪ፤ ለአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ አባላቶች አራት ቢሊዮን ብር የሚፈጅ የመኖርያ ቤት ሊገነባ መሆኑን ከንቲባው ከተናገሩ ወራት ቢቆጠሩም እስካሁን ተግባራዊ አለመደረጉ በአባላቱ ዘንድ ቅሬታን እየፈጠረ ነው ተብሏል።
ለኮንዶሚኒየሙ ግምባታ የቤት ዲዛይ፣ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን  ከአንድ ዓመት በፊት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በኮሚሽኑ ዋና መስሪያ ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይፋ ማድረጋቸው አይዘነጋም።
ከዐሥራ ሁለት ወራት በፊት በከተማ አስተዳደሩ እቅድ መሠረት ይህን ይባል እንጂ እስከ አሁን ድረስ ግን ምንም አይነት ግንባታ እየተከናወነ አልተጀመረም። ለዚህ ደግሞ ምክንያት የሆነውን ነገር ከተማ አስተዳደሩም ሆነ ፖሊስ ኮሚሽኑ አለመግለጹ በፖሊስ አባላቱ ዘንድ ቅሬታን እንደፈጠረ ኢትዮጵያ ነገ ከተለያዮ አባላት ያሰባሰበው አስተያየት መረዳት ተችሏል።

LEAVE A REPLY