ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ማለዳ ሱዳን ካርቱም ገቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ማለዳ ሱዳን ካርቱም ገቡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ወደ ሱዳን ዛሬ ማለዳ መጓዛቸው ታወቀ።

ዶክተር ዐቢይ በካርቱም በሚኖራቸው ቆይታ ከሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሌተናል ጄነራል አብዱል ፈታህ አልቡርሀንና ከጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ጋር በአገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ውይይት እንደሚያካሂዱ ተሰምቷል።
 የሱዳን ዜና አገልግሎት ሱዳን እንደዘገበው ከሆነ የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮም ዛሬ ለይፋዊ ጉብኝት ካርቱም ይገባሉ።
የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው የሱዳን መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከሆኑት ከጠቅላይ ሚኒስትሩና ከሉዓላዊ ምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ጋር ውይይት እንደሚያደርጉም  መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና በሱዳን ባለሥልጣናት መካከል የሚደረገው ውይይት ሱዳን ለምታደርገው ዴሞክራሲያዊ ሽግግር አሜሪካ በምትሰጠው ድጋፍ፣ ሱዳን ሽብርን ከሚደግፉ አገራት ዝርዝር ውስጥ ስለምትወጣበት ሁኔታና ሱዳን ከእስራኤል ጋር ስላላት ግንኙነት ላይ ያተኮረ መሆኑም እየተነገረ ነው።
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ሱዳን ባቀኑበት እለት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፒዮ ወደ ካርቱም እንደሚገቡ መነገሩ፤ በሁለቱ መካከል ውይይት ለማድረግ የሚያስችል እድል እንዳለም ግምቶች እየተሰነዘረ ነው።
 ከወራት በፊት በአሜሪካ አደራዳሪነት በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብጽ መካከል ሲካሄድ የነበረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ድርድር ጉዳይ በዚሁ አጋጣሚ ሊነሳ እንደሚችልም ፍንጮች ታይተዋል።

LEAVE A REPLY