1.6 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ የወባ በሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ለተመረጡ ክልሎች ተከፋፈለ

1.6 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ የወባ በሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ለተመረጡ ክልሎች ተከፋፈለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የወባ በሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ግብዓቶች አሰራጭቻለሁ አለ።

ግብዓቶቹ የወባ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያግዙ ኬሚካሎች፣ የመከላከያ አጎበሮችና የወባ መድኃኒቶች መሆናቸውም ተሰምቷል።
ከ889 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው 928 ሺኅ 000 ኪሎ ግራም የወባ መከላከያ ኬሚካሎች እና ከ461 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የወባ መድኃኒቶች መከፋፈላቸውን ኤጀንሲው አረጋግጧል።
በጋምቤላ፣ በቤንሻንጉል፣ በደቡብ፣ በአፋር፣ በትግራይ እና በአማራ ክልሎች ለሚገኙ 150 ወረዳዎች 314 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ 5.9 ሚሊዮን አጎበሮች እንደተሰራጩ ዛሬ ይፋ የሆነው መረጃ ያሳያል።

LEAVE A REPLY