ሀጫሉ ሲገደል አብራው የነበረችው ላምሮት ከማል ላይ ዐቃቤ ህግ ክስ እንዲመሰርት ተፈቀደለት

ሀጫሉ ሲገደል አብራው የነበረችው ላምሮት ከማል ላይ ዐቃቤ ህግ ክስ እንዲመሰርት ተፈቀደለት

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ሀጫሉ ሁንዴሳ በተገደለበት ምሽት በገላን ኮንዶሚኒየም አካባቢ አብራው የነበረችው ላምሮት ከማል ላይ ዐቃቤ ህግ በ15 ቀናት ውስጥ ክስ እንዲመሰርት ፍርድ ቤቱ አዘዘ።

ጉዳዩን ለተመለከተው በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ አራዳ ተረኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት  ምርመራ ማጠናቀቁን የገለጸው ፖሊስ መዝገቡን ለዐቃቤ ህግ አስረክቧል።
ይህን ተከትሎም ፖሊስ ዐቃቤ ህግ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ 109 መሰረት 15 ቀን ክስ መመስረቻ ጊዜ ይሰጠኝ ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።
“አርቲስት ሃጫሉ ጓደኛዬ ነው፣ በወቅቱ አብሬው ነበርኩ፣ ይህንን አልክድም፣ ለህይወቴ ሳልሳሳ ወንጀለኞቹን አሳይቻለሁ፣ ፍርድ ቤቱ የቤተሰቦቼ ማኅበራዊ ሕይወት እንዳይሰተጓጎል በዋስ ይልቀቀኝ” ስትል ዛሬ ለአራተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረበችው ላምሮት ከማል ችሎቱን ጠይቃለች።
ፍርድ ቤቱም በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ 63 መሰረት ጉዳዩ የግድያ ወንጀል የተፈፀመበት በመሆኑና ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት ክስ ሲመሰረት፤ ከ15 ዓመት በላይ እስራት የሚያስቀጣ በመሆኑ ዋስትና የሚያስከለክል ነው በማለት የዋስትና ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል።
ይሁን እንጂ ዐቃቤ ህግ በ15 ቀን ውስጥ ክስ ካልመሰረተ ተጠርጣሪዋ የዋስትና ጥያቄ አቤቱታን ማቅረብ እንደምትችል ፍርድ ቤቱ ገልጿል።

LEAVE A REPLY